1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጀርመን የመጀመሪያው ጥቁር የባቡር ሾፌር

ዓርብ፣ መጋቢት 6 2016

ኩዋን ማርቲን ዲቦቤ ምናልባትም ጀርመን ውስጥ በደንብ የሚታወቀው በሀገሪቱ የመጀመሪያው ጥቁር የባቡር ሾፌር በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በ1900ዎቹ ምን ያህል በቴክኖሎጂ ተራምደን እንደነበር ሳያሳይ አይቀርም፡፡ ምናልባትም ከዛሬ ሁኔታም በተሻለ ሁኔታ ፡፡

https://p.dw.com/p/4ddKm
Teaser Shadows of german colonialism AMH
ምስል DW

ኩዋን ማርቲን ዲቦቤ ምናልባትም ጀርመን ውስጥ በደንብ የሚታወቀው በሀገሪቱ የመጀመሪያው ጥቁር የባቡር ሾፌር በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በ1900ዎቹ ምን ያህል በቴክኖሎጂ ተራምደን እንደነበር ሳያሳይ አይቀርም፡፡ ምናልባትም ከዛሬ ሁኔታም በተሻለ ሁኔታ ፡፡  ያ በእግጥ ለእርሱ መንገድ ሆኖታል፡፡ በህይወቱ የገጠመው የተሻለ መንገድ፡፡

ዲቦቤ  በካሜሩን ዱዋላ በተባለች ስፍራ ተወለደ፡፡ ዘመኑ ደግሞ በጎርጎርሳውያኑ 1876፡፡ አባቱ የአካባቢውን ፖለቲካ ይመራ ነበር፡፡ ዲቦቤ ግን በ1890ዎቹ  አጋማሽ በርሊን ውስጥ በሚዘጋጀው ታላቁ አውደ ርዕይ ላይ ለመሳተፍ ወደ ጀርመን መጣ፡፡ የጉዞው ዓላማ ጀርመን "የገደብ የለሽ ዕድል ምድር" መሆኗን ለማሳየት ታሳቢ ያደረገ ነበር፡፡ ወቅቱ በቅኝ ግዛት ስር ያሉትን ማህበረሰብ ለጎብኚዎች ማሳየት የየእለት ተግባርም የሆነበት ጊዜ ነበር፡፡ ዛሬ ይህን የሰው ልጅ ለእይታ የሚቀርብበት ወይም የሰዎች ፓርክ (Human Zoo) ብለን እንጠራዋለን፡፡

ዲቦቤ በወቅቱ በርሊን ከደረሱ ከ100 በላይ አፍሪካውያን አንዱ ነበር፡፡ በወቅቱ  የጀርመን ቅኝ ግዛት አካላት ከነበሩ እንደ ናሚቢያ፣ ቶጎ፣ ታንዛንያ እና ካሜሩን ያሉ ሃገራት ተገደው የመጡት ዲቦቤ እና  የተወሰኑት ጓደኞች በኃይል ተገደው የመጡ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ የክፍያ ቃል ተገብቶላቸው የተወሰዱ ናቸው፡፡ በዚህ ሰዎች ለእይታ በሚቀርቡበት የአውደ ርዕይ መድረክ ዲቦቤ የ76 ቁጥር መለያ ተሰጥቶታል።

ዲቦቤ  በካሜሩን የሚሲዮን ትምህርት በመውሰዱ ጀርመንኛ በአግባቡ መጻፍና ማንበብ ይችል ስለነበር ከሌሎች ኋላ ቀር ማህበረሰብ ጋር  በጀርመን ሰዎች ለእይታ በሚቀርቡበት መድረክ ለመታየት በቂ ምክንያት አልነበረም ። ሲታይም ከአንዳቸውም ጋር መመሳሰል አይታይበትም ነበር።

አውደ ርዕዩን ለመመልከት በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ7 ሚሊዮን በላይ ጀርመናውያን ወደ ፓርኩ እንደጎረፉ ይነገራል።

 የአፍሪካውያን ምግብ አሰራር፣ ጭፈራ እና አደን ለማሳየት በተዘጋጀው (አውደ ርዕይ) ጎብኚዎች ዲቦቤ   እና ባልደረቦቹን  በግርምት ይመለከታሉ፡፡ መቀመጫውን በርሊን ያደረጉት የታሪክ አጥኚ ካታሪና ኦጉንቶዬ እንደሚሉት ይህ ቅኝ ግዛትን የማበረታታት ፕሮፓጋንዳ ሁነኛ አካል ነው፡፡

«በወቅቱ እንደ የጀርመን ቅኝ ግዛት ማህበረሰብ ያሉ የቅኝ ግዛት ማበረታቻ ፕሮፓጋንዳ ላይ የሚሰሩ ክለቦች እና በመንግስት የሚመሩ ድርጅቶች ነበሩ፡፡ የዚህ ተግባር ዋና ዓላማ የቅኝ ግዛት ያስፈልገናል የሚል አስተሳሰብን በሁሉም ተራ ጀርመናውያን አዕምሮ ውስጥ ማስረጽ ነበር፡፡ እንደ ዛሬ ሳይሆን ያኔ አብዛኛው ሰው  ከአውሮጳ ውጪ ስላለው ዓለም እምብዛም እውቀቱ የለውም፡፡ እናም በመጀመሪያ ቅኝ ግዛት ሁሉም እንደ አገር የሚስማማበት ትልቅ ቁምነገር መሆኑን የሚያሳምን ሃሳብ መሸጥ አስፈልጓል፡፡»

የስልጣኔ ተልእኮ፣ ዘረኝነት፣ ሳንሳዊ ዘረኝነት፣ ጀርመን አፍሪካውያንን ቅኝ ለመግዛት መብት እንዳላት ጀርመናውያኑን ለማሳመን አውደ ርዕዩ አንድ ማሳያ መንገድ ነው፡፡ ዲቦቤ እና ከሱ ጋር የመጡ ሌሎች በርካታ ሰዎች የጀርመን ተማሪዎች ስለ ሰው የዘር ሳይንስ ሲያጠኑ ቤተሙከራ እንዲቀርቡ የተደረጉ ሰብዓዊነታቸው ተገፈፈባቸው፡፡ በሀሰተኛ ሳይንስ  የሰው ዘረመል ጥራት ጥናት እንዲደረግባቸውም ሆነ፡፡

እንደዚያም ሆኖ ግን ከሰብዓዊነት ከወረደው አያያዝ ባሻገር ግን ዲቦቤ አሁንም በቤርሊን መቆየትን ምርጫው አድርጓል፡፡ በርግጥ በትክክል በዚህን ጊዜ ምን እንደ ተፈጠረ የሚታወቅ ነገር አልነበረም፡፡ የሚታወቀው ዲቦቤ በጀርመኗ መዲና በተሰጠው ስልጠና የእጅ ስራ ባለሙያ ለመሆን መብቃቱ ብቻ ነው፡፡ ካተሪና እንደሚሉት ይህ በእርግጥ የተለመደ ነው ። 

«ሰዎች መጀመሪያ ላይ ስለ አፍሪካውያኑ ለማወቅ ከፍተኛ ጉጉት ነበራቸው፡፡ እነዚህ  ከሌላ ባህላዊ ዘልማድ የመጡ አስገራሚ ህዝብ ናቸው ብለውም ይመለኩቱአቸዋል፡፡ በተለይም በበርሊን እንዲህ ነበር፡፡ በሌሎች የጀርመን ከተሞችም በመጀመሪያ ከፍተኛ ተቀባይነት ነበራቸው፡፡ በርግጥ በአፍሪካውያኑ ላይ ጥቃት የተፈጸመባቸው አጋጣመሚዎችም ነበሩ፡፡ ግን ደግሞ እንደ ማንኛውም በትክክለኛ አስተሳሰብ እንደ መደበኛ ህዝብ ተመልክተው የተቀበሉዋቸውም በርካቶች ነበሩ፡፡ እንደውም አንዳንዶቹ ቤተሰብም አድርጓቸዋል፡፡ ተጋብተው ቤተሰብ ያፈሩም ጥቂት አይደሉም፡፡ »

በ1902 ዲቦቤ በበርሊን የባቡር ሾፌር ሆነ፡፡ በወቅቱ በጀርመን የተስፋፋው ዘረኝነት ዲቦቤን በጉጉትና በግርምት ለማየት ካለው ፍላጎት ጋር ተዳምሮ በጣም ታዋቂ አድርጎታል፡  ቆየት ብሎም ዲቦቤ  እንዲህ ሲል ጽፎ ነበር ።

"ጠንክሬ በመስራትና በመልካም ጸባይ ታማኝነት አትርፌአለሁ”

ካተሪና ኦጉንቶዬ እንደሚሉት በመጀመሪያ ላይ ጀርመን የደረሱ አፍሪካውያን እምብዛም የቅኝ ግዛቱ ተጠቂ አልነበሩም፡፡ ይልቁኑ በቀላሉ ከማህበረሰብ ጋር መቀላቀል ችለው ነበር።