1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በዋግ ህምራ ዞን ጎርፍ የመንገድ ጉዳት አስከትሏል

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 25 2016

ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመንገድ ብልሽት በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በትራንስፖርት ፍሰቱ ላይ ጫና መፍጠሩን ብሔረሰብ አስተዳደሩ አስታውቋል፣ በሌላ በኩል በጎርፍ ምክንያት ለሁለት ሳምንታት ተቋርጦ የነበረው የሞጣ ባህር ዳር መንገድ ተጠግኖ አገልግሎት መጀመሩን የእነማይ ወረዳ አመልክቷል፡፡

https://p.dw.com/p/4k8Rw
Äthiopien | Straße in Wahgmra durch Überschwemmung zerstört
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

ዋግህምራ ዞን የመንገዶቾ በጎርፍ መጎዳት መጓጓዛውን አስተጓጉሏል

በዋግኽምራ ዝናብ በት/ ቤቶችና በመንገዶች ላይ ጉዳት አስከተለ

ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመንገድ ብልሽት በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በትራንስፖርት ፍሰቱ ላይ ጫና መፍጠሩን ብሔረሰብ አስተዳደሩ አስታውቋል፣ በሌላ በኩል በጎርፍ ምክንያት ለሁለት ሳምንታት ተቋርጦ የነበረው የሞጣ ባህር ዳር መንገድ ተጠግኖ አገልግሎት መጀመሩን የእነማይ ወረዳ አመልክቷል፡፡

በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ከፍያለው ደባሽ ለዶቼ ቬሌ በስልክ እንደገለጡት ከነሐሴ ወር መጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ በአካባቢው እየጣለ ያለው ዝናብ ባስከተለው ጉዳት በሁለት ወረዳዎች ከ50 በላይ ትምህርት ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

በዋግህምራ ሁለት ወረዳዎች «ሰሚ አጥተዋል» መባሉ

ክረምቱ ከባድ በመሆኑ በተለያዩ ወረዳዎች ጉዳት መድረሱን የጠቀሱት አቶ ከፍያለው፣ በሰቆጣ ወረዳ 26 ትምህርት ቤቶችና በጋዝጊብላ ወረዳ በተመሳሳ 28 ትምህርት ቤቶች በከባድ ዝናብ ምክንት ፈርሰዋል ነው ያሉት፡፡

ዝናቡ በመንገዶች ላይም ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የሚገልፁት አቶ ከፍያለው ከኮረም ሰቆጣና ከአበርገሌ ሰቆጣ መንገደኞች በቅብብሎሽ የትራንስፖርት አገልግሎት እያገኙ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

ከኮረም ተነስቶ ወደ ብሔረሰብ አስተዳደሩ ማዕከል ሰቆጣ የሚወስደው መንገድ በጭቃ ምክንያት ለትራንስፖርት አገልግሎት አስቸጋሪ መሆኑንም ኃላፊው አመልክተዋል፡፡ ከአበርገሌ ኒሯቅ ከተማ ወደ ሰቆጣ በቀጥታ ለመምጣት መንገዱ በጎርፍ መበበላሸቱ የትራንስፖርት አገልግሎቱ በቅብብሎሽ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡ የህም ተገልጋዮቹን ለከፍተኛ እንግልት እየዳረጋቸው መሆኑን ነው አቶ ከፍያለው የተናገሩት፡፡

ዋግህምራ ዞን የመንገድ መበላሸት ማህበራዊ ችግር አስከትሏል
ከኮረም ተነስቶ ወደ ብሔረሰብ አስተዳደሩ ማዕከል ሰቆጣ የሚወስደው መንገድ በጭቃ ምክንያት ለትራንስፖርት አገልግሎት አስቸጋሪ መሆኑንም ኃላፊው አመልክተዋል፡፡ ከአበርገሌ ኒሯቅ ከተማ ወደ ሰቆጣ በቀጥታ ለመምጣት መንገዱ በጎርፍ ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የአበርገሌና የጻግብጂ ወረዳ ነዋሪዎች ሮሮ

በተለይ ከዳህና ወረዳ ወደ ሰቆጣ ከተማ ህመምተኞችን ማጓጓዝና የንግድ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንዳልተቻለ ኃላፊው ተናግረዋል፤ ይህም በብሔረሰብ አስተዳደሩ የእለት ከእለት እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ መፍጠሩን አስረድተዋል፡፡

ከዳህና ወረዳ ማዕከል አምደወርቅ ወደ ሰቆጣ የሚወስደው አውራ ጎዳና በእክጉ መጎደቱን የሚናገሩት ኃላፊው በተለይ የሚወልዱ እናቶችን ወደ ሰቆጣ ሆስፒታል ማድረስ አልተቻለም፣ አፋጣን ህክምና የሚሹ ህመምተኞችም ወደ ጠና ተቋማት መድረስ አልቻሉም ነው ያሉት፡፡ ጭነት የጫኑ መኪናዎችም ወደ ከተማዋ መግባት ባለመቻላቸው በንግድ እንቅስቃሴው ላይ ቻና መፍጠሩን አመልክተዋል፡፡

በድርቅና ረሃብ ለተጎዱ ወገኖች እርዳታ የማሰባሰቢያ ዘመቻ

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአዲስ አበባ፣ ሞጣ ባህርዳርና ከቢቸና ደብረማርቆስ የሚወስደው አውራ ጎዳና ከሁለት ሳምንት በላይ በብልሽት አገልግሎቱ ተቋርጦ መቆየቱን በክልሉ የምስራቅ ጎጃም ዞን እነማይ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደጉ አየነው ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው እንዳሉት በወረዳው ልዩ ስሙ “ዲቢሳ” በተባለ ቦታ ላይ የነበረ አነስተኛ ድልድይ በጎርፍ በመወሰዱ የትራፊክ ፍሰቱ ተቋርጦ የቆየ ቢሆንም አሁን መንገዱ ተጠግኖ ከቅዳሜ ነሐሴ 25/2016 ዓ ም ጀምሮ መንገዱ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

በዚህ ክረምት እየጣለ ባለው ከባድ ዝናብ በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ናዳዎችና የመሬት መንሸራተት አደጋዎች መድረሳቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፣ በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት፣ ጃንአሞራ፣ በየዳና አዲአርቃይ ወረዳዎች ብቻ በናዳና በመሬት መንሸራተት  የ23 ሰዎች ህይወት ማለፉ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ታምራት ዲንሳ