1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ የሀሰተኛና ጥላቻ ንግግሮችን የቃኘው ጥናት

ማክሰኞ፣ ሰኔ 13 2015

በኢትዮጵያ በተለይም በስፍት በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም የተሰራጨው የሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር ሁናቴ ጥናት ይፋ ሆነ፡፡ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ተጠንቶ ዛሬ ይፍ የተደረገው ዓመታዊ ጥናቱ፤ በሀሰትና ጥላቻ ላይ ተንተርሰው የተሰራጩ መረጃዎች አደገኝነትንም ገልጿል፡፡

https://p.dw.com/p/4SqSy
Uganda | Smartphone Nutzerin in Kampala
ምስል ISAAC KASAMANI/AFP/Getty Images

በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የጥላቻ እና የሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭት ክፉኛ ተስፋፍቷል

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አከናወንኩ ባለው ስድስት ወራትን በፈጀውና ዛሬ ይፋ በሆነው ጥናት፤ ከ1 ሺህ 800 በላይ ዳታ በመሰብሰብ በግብዓትነት ተጠቀምኩ ብሏል፡፡ በዚህም የሀሰተኛ እና የጥላቻ ንግግሮች በአራት መንገዶች ማለትም በተንቀሳቃሽ ምስል፣ በምስል፣ በድምጽ እና በጽሁፍ ሲሰራጩ ነበር ብሏል፡፡ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ከሁሉም በላቀ ደግሞ አምስት የማህበራዊ መገናኛ ዜዴ ፕላትፎርሞች መሰል መረጃዎችን በግንባር ቀድምትነት ሲያሰራጩ መሰንበታቸውን ጥናቱ አመልክቷል፡፡ አቶ ታምራት ደጀኔ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የስትራቴኪክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ናቸው፡፡ “ፌስቡድ፣ ቲክቶክ፣ ቴሌግራም፣ ዩቲዩም እና ቲዊተር ሀሰተኛ እና የጥላቻ ንግግሩ በጉልህ የተሰራጨባቸው ናቸው፡፡ በዚህም ጥላቻን የሚስፋፉ፣ ብሔር እና ሃይማኖትን የሚያንቋሽሹ እንዲሁም ግለሰቦች ላይ ያተኩሩ የጥላቻ እና ሀሰተኛ መረጃዎች በብዛት የተሰራጨባቸው ሆነው አግኝተናቸዋል፡፡ በጋዜጠኝነት ሙያ የተከለከሉ የምስል እና የጽሁፍ መረጃዎች በተለይም በብዛት ተሰራጭተውባቸዋል፡፡ ግጭት ቀስቃሽ መረጃዎችም በጉልህ ተዘዋውረውባቸዋል፡፡”

Symbolbild Soziale Netze
የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችምስል Axel Heimken/dpa/picture alliance

ይህ ጥናት እነዚህ ሳይጣሩና ሀሰት ላይ ተመስርተው ይሰራጫሉ የተባሉ መረጃዎቹ ምንጮቻቸው ማነው የሚለውም በጥናቱ ለመዳሰስ ተሞክሯል ተብሏል፡፡ “ግለሰቦች፣ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች እና ተጽእኖ ፈጣሪ ነን ያሉ ሰዎች በስርጭቱ ተሳትፈዋል፡፡”

የጥላቻ ንግግሮ እና ሀሰተኛ መረጃዎቹ መገለጫዎችስ ምንድናቸው የተባሉት አቶ ታምራት፤ “እርሰ ብርስ የሚያጋጩ፣ አንድነትን የሚንዱ ስድቦች፣ ክብረነክ ንግግሮች፣ እውነታን መካድ፣ ታሪክን መነሻ አድርገው ጥላቻን የሚነዙ ይገኙበታል፡፡ በጥናቱ ከማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎቹ ግጭትን የሚያባብሱ ገጾችን ከህጋቸው ጋር በሚጣረዝ መልኩ ታግሰው የተገኙም በመስተዋላቸው ወደፊት የተሻለ ግንኙነት በመፍጠር ቢያንስ መሰል ህጎቻቸውን እንኳን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ለማስገንዘብ አቅደናል፡፡”

እነዚህን የጥናት ግኝቶች በመንተራስም ባለስልጣኑ በቀጣይ እሰራቸዋለሁ ያሏቸውን እቅዱንም በዚህ ጥናት ማጠቃለያ አስቀምጧል፡፡ “ማህበራዊ ሚዲያ የሚመራበትን የፖሊሲ ማዕቀፍ ማዘጋጀት አንዱና ዋነኛ ስራችን ይሆናል፡፡ የጥላቻ እና ሀሰተኛ መረጃዎች ህግ ብኖርም አፈጻጸም ላይ ክፍተት በመስተዋሉ ደንብና መመሪያ እንዲዘጋጅለትም ይሆናል፡፡ ሀሰተና እና የጥላቻ ንግግሮችን የሚለዩ ቴክኖሎጂዎችን ማዳበር ሌላው እንደ እልባት የተቀመጠ ሀሳብ ነው፡፡”

የጥላቻ እና ሀሰተኛ ንግግሮችን ለመከላከል የሚወጡ ህግጋት አንዳንዴም ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን እንዳይጎዳ ስጋታቸውን የሚያስቀምጡ አሉ፡፡ ታዲያ ይህ ጥናት በሚከናወንበት ወቅትና ለተግባር በተሰናዳበት ባሁን ወቅት ከዚህ ጋር እንዳይጋጭ ምን ያህል ትኩረት ተሰጥቶት ይሆና የተባሉት የጥናቱ አስተባባሪ እና አቅራቢ አቶ ታምራት ደጀኜ፤ “ሚዛናዊነት የሚጎድላቸው የሀሰት እና ጥላቻ አዘል መረጃዎች በራሳቸው ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ አውድን የሚጎዱ ቢሆንም የፕሬስ ነጻነት ላይ ግን አንዳችም ማንገራገር የለም” ሲሉ መልሰዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከ60 በላይ የዩቱዩብ ቻናሎች ፍቃድ ወስደው እንደሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን መረጃ ያሳያል፡፡ ባለስልጣኑ እየተስፋፋ ለመጣው የአዳዲስ የቴሌቪዥን እን ራዲዮ ማስፋፊያ ጥያቄዎችም አዎንታዊ ምላሾችን እየሰጠ መሆኑ ተነግሯል።

ሥዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ