በኢትዮ-ሱዳን ድንበር የሰዎች ዝውውር እና ችግሮቹ
ሐሙስ፣ መጋቢት 12 2011ማስታወቂያ
በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አካባቢዎች የሰዎች ዝውውርን ሕጋዊና ድህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ የሁለቱም መንግስታት ትኩረት ይሻል ተባለ፡፡ በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራንና የሚመለከታቸው የመንግስት ስራ ሐላፊዎች እንዲሁም የሱዳን ገዳሪፍ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንና የሀገሪቱ ባለስልጣናት የተገኙበት የጋራ የምክክር መድረክ በመቀሌ ተካሂዷል፡በምክክር መድረኩ ላይ እስካሁን በአካባቢው የሚደረግ የሰዎች እንቅስቃሴ ሕጋዊ ማዕቀፍ ስላልተበጀለት ለተለያዩ ሕገወጥ ተግባራት የተጋለጠ ነው ተብሏል፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ባለፊት 10 ዓመታት ብቻ ከኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 5 ሚልዮን በላይ ዜጎች በሕገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠው ተሰደዋል፡፡ ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ከመቀሌ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል። በትንሹ ባለፊት ዓመታት ከ1 ነጥብ 1 ቢልዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ከኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለሕገወጥ ደላሎች መከፈሉን ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ