1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል ሴቶችን በሥልጣን የማሳተፍ ጥያቄ

ሰኞ፣ የካቲት 22 2013

ሴቶችን በፖለቲካው ዘርፍ እኩል ተሳታፊ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት መልካም ጅምር ቢሆንም፣ በዝቅተኛው የመንግሥት መዋቅር አሁንም ጉድለቶች እንዳሉ የአማራ ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ አስታወቀ፣ የሴቶችን ተሳትፎ የሚያጎለብቱ በፖሊሲና በስልት የተነደፉ አሰራሮች ወደ ተግባር እንዲለወጡ ትግል አስፈላጊ ነው ተብሏል፡፡

https://p.dw.com/p/3q413
Äthiopien Amhara Frauen Liga
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የሴቶች የስልጣን ውክልና በታችኛው የስልጣን እርከን

ሴቶችን በፖለቲካው ዘርፍ እኩል ተሳታፊ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት መልካም ጅምር ቢሆንም፣ በዝቅተኛው የመንግሥት መዋቅር አሁንም ጉድለቶች እንዳሉ የአማራ ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ አስታወቀ፣ የሴቶችን ተሳትፎ የሚያጎለብቱ በፖሊሲና በስልት የተነደፉ አሰራሮች ወደ ተግባር እንዲለወጡ ትግል አስፈላጊ ነው ተብሏል፡፡  በባሕር ዳር ከተማ ዛሬ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ ላይ የተገኙት የኤፌድሪ ትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገሥ የሴቶችን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን እውን ለማድረግ በፖሊሲና በስልት ቢደገፍም ወደ ተግባር ለመቀየር ግን አሁንም ክፍተቶች እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡ በመጪው 6ኛው አገራዊ ምርጫም የአገሪቱ ሴቶች ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ