1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቻይና እና በአሜሪካ መካከል ውጥረት የቀሰቀሰው የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት

ሐሙስ፣ ሐምሌ 28 2014

የአሜሪካ የታችኛው ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በታይዋን ያደረጉት ጉብኝት በቻይና እና በአሜሪካ መካከል ውጥረት ቀስቅሷል። ቻይና የታይዋንን የባሕር ክልል በመጣስ ከባድ የጦር ልምምድ አድርጋለች። ሩሲያ የአፈ ጉባኤዋ ጉብኝት የአሜሪካ የተለመደ በአገሮች ሉዓላዊነት ጣልቃ የመግባት አባዜ መሆኑን በመጠቆም ከቻይና መወገኗን አሳይታለች።

https://p.dw.com/p/4F8MH
 Sea Guardians-2
ምስል Geng Haipeng/Xinhua/picture alliance

በቻይና እና በአሜሪካ መካከል ውጥረት የቀሰቀሰው የናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት

የአሜሪካ የታችኛው ምክርቤት  አፈጉባኤ ወይዘሮ ናንሲ ፔሎሲ ባለፈው ማክሰኞ በታይዋን ያደረጉት ጉብኝት የአሚሪክንና ችይናን ግኝኑነት ከመቼውም ግዜ ይበልጥ እንዳሻከረው እየተነገረ ነው።  ወይዘሮ ናንሲ የሚመሩትን የምክርቤት ልዑክ  ይዘው ወደ ታይዋን ሲያመሩ፤ ቻይና የጉብኝቱ አንደምታ የቻይናን ሉአላዊ ግዛት የሚጥስና የታይዋንን ተገንጣይ ሀይሎች የሚያነቃቃ ነው በማለት አጥብቃ በመቃወም የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ አስታውቃ ነበር።

አፈጉባኤ ፔሎሲና ቡድናቸው ግን የቻይናን ተቃውሞም ሆነ የአንዳንድ እሜሪካ ባለስልጣናትን ምክር ወደ ጎን በመተው፤ ጉብኝታቸውን ለአጭር ግዜም ቢሆን አሳክተው ተመልሰዋል። ለታይዋን ባለስልጣናትና ህዝብ ባደረጉት ንግግርም እሳቸውና ሉኡካቸው ወደ ታይዋን የመጡት አገራቸው ታይዋንን በምንም አይነት  ቢሆን እንደማትከዳት ለማረጋገጥ ነው ብለዋል።  

የአሁኗ ታይዋን የተመሰረችው እ እ እ 1949 ዓም በሊቀመንበር ማኢኦ ሴቱንግ የሚመራው የቻይና  ኮሚኒስት ፓርቲ ከስልጣን ባስወገዳቸው ቺያንግ ካይ ሼክ የስደት መንግስት እንደሆነ ይታወቃል።  14 ከመቶ የሚሆነውን የቻይና ህዝብ የያዘችው ታይዋን እ እ እ በ1971  ዓም ከመንግስታቱ ድርጅት አባልነት ተወግዳ፤ በቻይና እስከተካችበት ግዜ ድረስ በድርጅቱ ህጋዊ የቻይና ተወካይ ሆና ቆይታለች።

ፔኪንግ ግን ታይዋንን የግዛቷ አካል\አድርጋ የምጥቆጥር ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅትም ከ193 የመንግስታቱ ድርጅት አባል አገሮች በስራ አምስቱ ብቻ ነው ዕውቅና የተሰጣት። አሜሪካና ለሌች የምራባውያን አገሮች  ይፋዊ የሆነ አገራዊ እውቃና ባይሰጧትም ግንኑነታቸውና ትብብራቸው ግን የተለየ እንደሆነና በተለይ ቻይና በታይዋን ላይ ያላትን ጥያቄ በበጎ እይማያዩ ብቻ ሳይሆን፤ ደሴቲቱን በጦር መሳሪያ እንደሚያስታጡቁትና በአሁኑ ወቅት ደሴቲቱ 300 ሺ ዘመናዊ ጦር እንዳላት ነው የሚነገረው።   

Reaktionen auf Pelosi Taiwan Besuch
በቻይና የ82 ዓመቷ አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በታይዋን ያደረጉትን ጉብኝት የሚቃወሙ ሰልፎች ሲደረጉ በታይፔይ በአንጻሩ ቻይናን የሚተቹ ዜጎች አደባባይ ወጥተዋል።ምስል Ann Wang/REUTERS

የ82 አመቷ አፈጉባኤ ፔሎሲ በጉብኝታቸው ታይዋንን በቻይና አንጻር የዴሞክራሲና የኢኮኖሚ እድገት ተምሳሌት አድርገው ነው የሳሏት።”ታይዋን እራሷ እያበበ ያለ ዲመኦክራሲ ናት። ተስፋ ብርታትና ቆራጥነት ሰላምንና እድገትን ለማምጣት የሚያስችሉ አይነተኛ መስሪያዎች መሆናቸውን ያሳየች ናት ሲሉም ገልጸዋታል።  

ይሁን እንጂ ጉብኝቱ በተቃውሞና ውጥረት ታጅቦ ነው የተካሄደው። ቻይና ተቃውሙዋን በፔኪንግ የአሜሪካንን አምባሳደር አስጠርታ በግልጽ ያስታወቅች ሲሆን፤ ጉብኝቱ ታይዋንና  አሚሪካንንም ጭምር ዋጋ የሚያስክፈል መሆኑን ገልጻለች።  ወይዘሮ ፐሎሲ ገና ዋና ከተማ ታይፔንን ሳይለቁም፤ የጦር ሰራዊቱ በታይዋን ዙሪያ የጦር ልምምድ እኒያደርግ ታዞ በእንቅስቃሴ ላይ ነው። ከቻይና  ወደ ታይዋን የሚገቡ አንዳንድ ሸቀጦች ላይም እገዳ መጣሉ ተስምቷል። ከዚህም በቀር የጦር ልምምዱና እንቅስቃሴው፤ ደሴቲቱን በከበባ ውስጥ እንዳያስገባትና  ይህም  አሜሪካንና ሌሎች ምዕራባውያንን ለግጭት የሚጋብዝ እንዳይሆን ያሰጋል ነው የሚባለው።፡የሰባቱ ባለጸጋ አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፤ ቻይና የአፈጉባኤዋን ጉብኝት አለዝባ እንድታየውና ውጥረቱን እንድታረግብ የሚጠይቅ መግለጫ ማውጣቸው የውጥረቱን ደረጃ የሚያመላክት ነው። 

Infografik - Chinesische Manöver vor Taiwan - EN
ቻይና በታይዋን ዙሪያ ከባድ ወታደራዊ ልምምድ እያደረገች ትገኛለች።

በአንጻሩ ሩሲያ ይህ የአሜሪካ ድርጊት የተለመደ በአገሮች ልኡላዊንት ላይ  የመግባት አባዜ ነው በማለት ከቻና ጎን የምትቆም መሆኑን አሳውቃለች። አንድንዶች አሜሪካና ቻይና በታይዋን ላይ ያላቸውን ልዩነትና ውዝግብ ምዕራባውያን በዩክሬን ምክኒያት ከሩሲያ ጋር ከገቡበት ውዝግብ ጋር ያመሳስሉታል። ሚስተር ሚኬል ዴስዊን በኩዌንስ ኢንስቲቱት የምስራቅ እስያ ዳይሬክተር ግን በዚህ አይስማሙ፣እሳቸው፤ ሁለቱ ምናልባት ተመሳሳይነት ሊኖራቸው ይችል እንደሆን እንጂ አንድ  አይደሉም ነው የሚሉት፤ “ በመሰረቱ  የፖለቲካ ስሌቱ፣ ተሳታፊ የሆኑት መንግስታትና ፍላጎታቸውም በጣም የተለያየ ነው። ስለዚህ በሩሲያና ዩክሬን የተፍጠረውን ከቻይናና ታይዋን ሁኒታ ጋር  ማመሳስሉ ትክክል ያልሆነና  አሳስችም ነው በማለት ነው የሚከራከሩት። 

የወይዘሮ ፔሎሲና ቡድናቸው የታይዋን ጉብኝት በታይዋን ዴሞክራሲና እድገት በመመሰጥ ሳይሆን ይልቁንም ቻይና  በአካባቢው የምታደርገውን መስፋፍትና መጎልበትም ለመገዳደር እንደሆነ ነው የሜነገረው። በዚህም ዴሞክራቷ ናንሲ ፔሎሲ የአብዛኛዎቹን የአገራቸውን ዴሞክራቶችና የሪፐብሊካኖችንም አድናቆትና ድጋፍ እንዳገኙ ነው እየተገለጸ ያለው። ባንጻሩ ይህ ግብኝት ቻይናንም እንድታከርና ወደ ግጭት ሊመራ ወድሚችል እንቃስቃሴ  እንድተግባ እንዳይገፋፍትና በሩቅ ምስራቅ እስያም ሌላ የግጭት ቀጠና እንዳይፈጠር የሚሰጉ ወገኖች፤ የአፈጉባኤዋ ጉብኘትን ትርፋማነት እየጠየቁ ነው።  

ገበያው ንጉሴ
እሸቴ በቀለ
ኂሩት መለሰ