1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሶስት ክልሎች በጎርፍ መጥለቅለቅ ጉዳት ደረሰ

ዓርብ፣ ነሐሴ 29 2012

በኢትዮጵያ ከወትሮ ለየት ባለ መልኩ ጠንክሮ የሰነበተው የክረምቱ ዝናብ በተለያዩ ክልሎች የጎርፍ መጥለቅለቅ አስከትሏል። ሰሞኑን በኦሮሚያ ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች የወንዞች ሙላትን ተከትሎ በተፈጠረ የጎርፍ መጥለቅለቅ በርካቶች ከመኖርያ ከቄዬአቸው ተፈናቅለዋል፤ በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።

https://p.dw.com/p/3i0lY
Äthiopien | Überschwemmungen des Fluss Awash
ምስል DW/S. Getu

በኢትዮጵያ ከወትሮ ለየት ባለ መልኩ ጠንክሮ የሰነበተው የክረምቱ ዝናብ በተለያዩ ክልሎች የጎርፍ መጥለቅለቅ አስከትሏል። ሰሞኑን በኦሮሚያ ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች የወንዞች ሙላትን ተከትሎ በተፈጠረ የጎርፍ መጥለቅለቅ በርካቶች ከመኖርያ ከቄዬአቸው ተፈናቅለዋል፤ በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱ ተነግሯል። በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጄሬ ወረዳ ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ዳዋ ኢሉ ወረዳ ፣ ምስራቅ ሸዋ ዞን ሊበን ወረዳ፣ አዳማ ፣ ከፊል ፈንታሌ ወረዳ፣ እንዲሁም የመተሃራ እና የመርቲ ከተሞች ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው። በአፋር ክልል የአፋምቦ፣ ድብቲ እና አሳኢታ ከተሞች እና አካባቢያቸው የጎርፍ መጥለቅለቅ የደረሰባቸው አካባቢዎች ናቸው። በአማራ ክልልም በተመሳሳይ ለተከታታይ ሳማንታት በጣለ ዝናብ የጎርፍ መጥለቅለቅ እና የመሬት መንሸራተት አስከትሏል። ኢንሳሮ እና አንኮበር በተባሉ አካባቢዎች አምስት ሰዎች በጎርፍ ተወስደው ሕይወታቸው አልፏል። በዚህም በሰሜን ሸዋ ዞን ከ8,000 ሄክታር በላይ የእርሻ ማሳ ላይ ጉዳት ሲደርስ  ከ57,000 የሚልቁ አርሶ አደሮች የጉዳቱ ሰለባዎች ሆነዋል። በተጨማሪም 700 የመኖርያ ቤቶች መውደማቸውን እና ከ4500 በላይ ሰዎች በዚሁ ምክክንያት መፈናቀላቸውን የባልደረባችን አለምነው መኮንን ዘገባ ያመለክታል። 

Äthiopien | Überschwemmungen des Fluss Awash
ምስል DW/S. Getu
Äthiopien | Überschwemmungen des Fluss Awash
ምስል DW/S. Getu
Äthiopien | Überschwemmungen des Fluss Awash
ምስል DW/S. Getu

ታምራት ዲንሳ

አለምነው መኮንን

ስዩም ጌቱ

ነጋሽ መሀመድ