1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሲዳማ የመሬት መንሸራተት የ11 ሰዎች ህይወት አለፈ

ሰኞ፣ ሐምሌ 22 2016

በደቡባዊው የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመሬት መንሸራተት አደጋ በህይወት ላይ እያስከተለ የሚገኘው አደጋ እየተደጋገመ መጥቷል ፡፡ ባለፋው ሳምንት ከ230 በላይ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የጎፋው ዞን አደጋ ያስከተለው ሀዘን ባላገገመበት በአሁኑ ወቅት በሲዳማ ክልል ደግሞ ሌሊቱን ሌላ ተመሳሳይ አደጋ አስተናግዷል ፡፡

https://p.dw.com/p/4irtZ
Äthiopien - Erdrutsch in Sidama
ምስል Bureau of Government Communications Affairs of Sidama Region

በሲዳማ ክልል ሌላ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሰብአዊ ጉዳት አደረሰ

በሲዳማ የመሬት መንሸራተት የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ 

በደቡባዊው የኢትዮጵያ አካባቢዎች የመሬት መንሸራተት አደጋ በህይወት ላይ እያስከተለ የሚገኘው አደጋ እየተደጋገመ መጥቷል ፡፡ ባለፋው ሳምንት ከ230 በላይ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የጎፋው ዞን አደጋ ያስከተለው ሀዘን ባላገገመበት በአሁኑወቅት በሲዳማ ክልል ደግሞ ሌሊቱን ሌላ ተመሳሳይ አደጋ አስተናግዷል ፡፡

አደጋው እሁድ ሌሊት ለሰኞ አጥቢያ ከሌሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ የተከሰተው በክልሉ ማዕካለዊ ዞን ወንሾ ወረዳ ግሽሬ ጉዱሞ ቀበሌ ውስጥ ነው ፡፡ አደጋው የተከሰተው በአካባቢው የጣለውን ዝናብ ተከትሎ መሆኑን አንድ የቀበሌው  ነዋሪዎ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል ፡፡

የጎፋው ዘግናኝ የተፈጥሮ አደጋ

ሌሊቱን ለረጅም ሰዓታት ዝናብ ሲጥል መቆየቱን የጠቀሱት የቀበሌው የአይን እማኝ “ በድንገት በከፍታ ቦታ የነበረው አፈር ተደርምሶ በጎጆ ቤቶች ላይ ወደቀ ፡፡ ከሟቾቹ መካከል አንድ አባት ፣ ሁለት እናቶችና ህጻናት ይገኙበታል “ ብለዋል ፡፡

የአደጋው መጠን

አደጋው በምሽት በመከሰቱ የመሬት መንሸራተት ጠቋሚ ምልከቶችን የማየት ዕድል እንዳይኖር ማድረጉን ለዶቼ ቬለ የተናገሩት በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን  የወንሾ ወረዳ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ካያሞ ኪሚቢቻ “ አደጋው የደረሰው በሁለት መኖሪያ ቤቶች ላይ ነው ፡፡ በአጠቃላይ በአደጋው የሞቱት አሥር ሰዎች ናቸው ፡፡

እስከአሁን የስምንቱ አስክሬን የተገኘ ሲሆን የሌሎች ሁለት ሰዎች  ግን አላገኘንም ፡፡ ምናልባት በጎርፍ ተወስደው ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለን ፡፡ በአደጋው  ሌሎች ስድስት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው ወደ ይርጋዓለም ሆስፒታል ተወስደው የህክምና ዕርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል ፡፡ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል የሁለቱ ከባድ ጉዳት ሲሆን የአራቱ ግን መለስተኛ መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ገልጸውልናል ፡፡በተጨማሪም በአደጋው የቤት አንስሳትና የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶች ንብረት ወድሟል  “ ብለዋል ፡፡

«በጎፋ ወረዳው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች የአስቸኳይ ግዜ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።»

ቀጣይ ሥጋትና ጥንቃቄ

በደቡባዊ ኢትዮጵያ አካባቢ በሚገኙ ክልሎች በክረምት ወቅት መሰል የመሬት መንሸራተት አደጋዎች የሚከሰቱ ቢሆንም ዘንድሮ ግን የክስተቱም ሆነ የጉዳቱ መጠን ጨምሮ ነው የተስተዋለው ፡፡ አሁን ላይ በቀጣይ ቀናት በአብዛኛው የእገሪቱ አካባቢዎች ከመደበኛ በላይ የዝናብ ሥርጭት እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ሜትሮሎዎጂ ተቋም አስታውቋል፡፡

የዝናብ ሥርጭቱ ለሰብሎች ያለውን ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን የጠቀሱት በተቋሙ የሜትሮዎሎጂ ትንበያና ቅደመ ማስጠንቀቂያ   ዘርፍ  ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር አሳምነው ተሸመ “ ነገረ ግን  ህብረተሰቡ የመሬት መንሸራተትን ጨምሮ ከዝናብ ሥርጭት መብዛት ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ ከሚችሉ አደጋዎች ተገቢው ጥንቃቄ እንዲያደርግ “ በማለት መክረዋል ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የተጎጂ ቤተሰቦችን አጽናንተዋል ፡፡

በደቡባዊ ኢትዮጵያ አካባቢ ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ ከመሬት መንሸራተት ጋር በተያያዘ በጎፋ ዞን ከ230 በላይ  ፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 3 ፣ ትናንት ደግሞ በሲዳማ ክልል የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል ፡፡

ፎቶ ከሲዳማ ክልል የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ