1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሱዳን ጎርፍ መጥለቅለቅ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 112 ደረሰ

ሰኞ፣ ነሐሴ 30 2014

ሱዳን ዉስጥ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በደረሰ ሌላ ድንገተኛ ጎርፍ አደጋ ተጨማሪ 12 ሰዎች መሞታቸዉ ተነገረ። የሱዳን ባለስልጣናት ዛሬ ይፋ ባደረጉት መረጃ መሰረት፣ በሃገሪቱ የዝናቡ ወቅት ከጀመረበት ከግንቦት ወር ጀምሮ ባለዉ ጊዜ በተከሰተዉ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ እስካሁን 112 ሰዎች ሞተዋል።

https://p.dw.com/p/4GRpf
Flood in Sudan
ምስል Sami Alopap/AA/picture alliance

ሱዳን ዉስጥ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በደረሰ ሌላ ድንገተኛ ጎርፍ አደጋ ተጨማሪ 12 ሰዎች መሞታቸዉ ተነገረ። የሱዳን ባለስልጣናት ዛሬ ይፋ ባደረጉት መረጃ መሰረት፣ በሃገሪቱ የዝናቡ ወቅት ከጀመረበት ከግንቦት ወር ጀምሮ ባለዉ ጊዜ በተከሰተዉ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ  እስካሁን 112 ሰዎች ሞተዋል። በአደጋዉ የሚሞተዉ ሰዉ ቁጥር እየጨመረ ነው ሲሉም አስጠንቅቀዋል። የሱዳን ብሔራዊ የሲቪል መከላከያ ምክርቤት ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄኔራል ኧብዱል ጃሊል ኧብዱል ራሚን እንደተናገሩት በሃገሪቱ ያላማቋረጥ እየተከሰተ በሚገኘዉ የዉኃ መጥለቅለቅ እስካሁን 115 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። 
በሱዳን ከዚህ ቀደም ባልተለመደዉ ጊዜ ቀደም ብሎ የጀመረዉ የዘንድሮዉ የዝናብ ወቅት በሃገሪቱ ዙርያ ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶችን እና የመንግስት ተቋማት ብሎም የመኖርያ ቤቶችን በአጠቃላይ 85,000 ቤቶች ወድመዋል ብለዋል።  ቃል አቀባዩ እንደተናገሩት 74 ሰዎች በዉኃ ዉስጥ ሰምጠዉ ሕይወታቸዉ አልፏል፤ 32 ሰዎች ደግሞ በዉኃ መጥለቅለቅ ቤታቸዉ ላያቸዉ ላይ በመፍረሱ ሕይወታቸዉን ያጡ ናቸዉ፤ ስድስት ሰዎች ፤ በዉኃ መጥለቅለቁ ምክንያት  ባጋጠመ የኤሌትሪክ አደጋ ሕይወታቸዉን ያጡ ናቸዉ ብለዋል። 
በሱዳን ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ መከሰቱን ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ባለፈዉ ሳምንት ባወጣዉ መግለጫ በጎርፉ ቢያንስ 258,000 ሰዎች ተጎድተዋል። ሱዳን ካልዋት 18 ግዛቶች መካከል በ15 ቱ የጎርፍ አደጋ ጉዳት ማድረሱም አያይዞ ጠቅሷል። 
 

 

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ