1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የድረሱልን ጥሪ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 12 2015

በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን በአደገኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ፤ ብሎም የሚበላ የሚጠጣ ከማጣታቸዉም በላይ ምንም አይነት መረጃን እንደማያገኙ ተናገሩ። በታጣቂ ሚሊሺያዎች ንብረታችንን እየተዘረፉ ነዉ ያሉት ዜጎች ከሁሉ በላይ ግን እያስጨነቀን ያለዉ እቤታችን ቁጭ ብለን በተባራሪ ጥይት መድፍ አልያም የአዉሮፕላን ጥቃት ሰለባ እንዳንሆን ነዉ ብለዋል።

https://p.dw.com/p/4QMWv
Sudan Khartum | Kämpfe zwischen Armee und RSF-Miliz
ምስል AFP

«የኢትዮጵያ ህዝብ ይፀልይልን፤ የኢትዮጵያ ኤምባሲም ሳይቀር ተዘርፏል»

በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን በአደገኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገለፁ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ በሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን እንዳሉት የሚበላ የሚጠጣ ከማጣታቸዉም በላይ በተባራሪ ጥይት ጉዳት እየደረሰባቸዉ፤ ከዝያም አልፎ በታጣቂ ሚሊሺያዎች እጃቸዉ ላይ የያዙትን ንብረት እየተዘረፉ ነዉ። ከሁሉ በላይ ግን እያስጨነቀን ያለዉ እቤታችን ቁጭ ብለን የተባራሪ ጥይት እና የመድፍ አልያም የአዉሮፕላን ጥቃት ሰለባ እንዳንሆን ነዉ ብለዋል። 

በሱዳን መዲና ካርቱምን ጨምሮ በተለያዩ የሱዳን ከተሞች በሱዳን ጦር ሠራዊት እና የፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት መካከል ባለፈዉ ቅዳሜ የጀመረዉ ዉግያ ዛሬም ለስድስተኛ ቀን እንደቀጠለ ነዉ። ከምግብ ከሚጠጣ ዉኃ ችግር ባሻገር በታጣቂ ሚኒሽያዎች እየተዘረፍን ነዉ ያሉ በሱዳን በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ናቸዉ።

«ከምግብ እና የሚጠጣ ዉኃ ብሎም የመብራት አገልግሎት ጉዳይ ይበልጥ የሚያሳስበን የተባራሪ ቦንብ እና ጥይት እንዲሁም የአዉሮፕላን ጥቃት ነዉ። እስካሁን በካርቱም ሦስት ኢትዮጵያዉያን መገደላቸዉን ሰምተናል። አደጋ በመሆኑ እስካሁን አስክሬናቸዉ አልተነሳም። በሰሜን ሱዳንም እንዲሁ ኢትዮጵያዉያን እንደተገደሉ ሰምተናል። ካርቱም የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ተዘርፏል። የአዉሮጳ ህብረት ተቋምም እንደተዘረፈ ሰምተናል። ታጣቂ ሚሊሽያዎች ዘረፋ እያካሄዱ ነዉ።»

Sudan Khartum | Flucht Bewohner vor Kämpfen
ከጥቃት እየሸሹ የሚገኙ የካርቱም ነዋሪዎች ምስል AFP

የብሔራዊ ቴሌቭዥን አገልግሎት ተቋርጧል ፤ መረጃን ከየት ነዉ የምታገኙት?

« መረጃ የምናገኘዉ ወደ ኢትዮጵያ እየደወልን ቤተሰቦቻችንን እየጠየቅን ነዉ።  በሱዳን ጋዜጠኛ  መስክ ላይ ሆኖ መስራት የሚችልበት አዉድ ላይ አይደለም የምንገኘዉ።» የኢትዮጵያ ኤንባሲን ለማግኘት ሞክሬ ነበር አልተሳካልኝም፤ በኢንባሲ በኩል ርዳታ ለማግኘት አልሞከራችሁም?

« የኤትዮጵያ ኤምባሲ ራሱ ከለላ የሚፈልግበት ጊዜ ላይ የነዉ የሚገኘዉ። ኤምባሲዉ እንደተዘረፈ መረጃ ደርሶል። የአዉሮጳ ህብረት መስርያ ቤትም እንዲሁ፤ ግን በዓይን አላረጋገጥንም።  ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዉያን ሱዳን ዉስጥ በስደት ላይ እንዳሉ ይነገራል። የኢትዮጵያዉያን ጉዳይ እንዴት ቢደረግ ይሻላል?

« መንግስት ቢaneስ ከካርቱም የምንወጣበትን መንገድ ቢያመቻችልን ጠይቁልን። በተረፈ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፀልይልን።»  ዶቼ ቬለ በሱዳን ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን መካከል የሦስት ልጆች እናት የሆነች እና በካርቱም የራስዋ የፀጉር መስርያ ቤት ያላትን ኢትዮጵያ አነግሮ ነበር። ኢትዮጵያዊትዋ እንደነገረችን የፀጉር መፈሸኛ ቤትዋ ተዘርፏል። በካርቱም የሚገኘዉ የኢትዮጵያዉያን ቤተ-ክርስትያን ጥቃት ደርሶበታል።

እንደ ፖለቲካ ተንታኞች ስልጣን በሚፈልጉ ሁለት ጀነራሎች የተቀሰቀሰዉ ጦርነት ማቆምያ ያለዉ አይመስልም። እንደዉም የዉጭ ሃገራትን በየረድፉ እንዳያሳለፍ እያሰጋ ነዉ።

ሙሉ ጥንቅሩን የድምጽ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ!

 

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ