1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በምዕራብ ወለጋ ዞን ወባ ህጻናትን እየገደለ ነው

እሑድ፣ ነሐሴ 21 2015

የሕክምና ባለሞያዎች ማክሰኞ ዕለት በዚሁ በሽታ 3 ህጻናት በአንድ ጤና ጣቢያ ህይወታቸው ማለፉን ጠቁመዋል፡፡ በብዛት ከ10 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በበሽታው እየተጠቁ እንደሚገኙም አክለዋል፡፡ የምዕራብ ወለጋ ዞን የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ጫላ በቆንዳላ እና ቤጊ ወረዳዎች የወባ በሽታ ጉዳት ማድረሱን አረጋግጠዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4VaUj
The mosquito has bitten through a fabric and sucks blood - a macro-photo Copyright: xAlexeyxRomanovx/xDesignxPicsx , 309
ምስል pzAxe/IMAGO

በምዕራብ ወለጋ ዞን ወባ ህጻናትን እየገደለ ነው

በምዕራብ ወለጋ  ዞን ቆንዳላና ቤጊ ወረዳ ውስጥ ወባ  ህጻናትን መግደሉን ነዋሪዎች ተናገሩ።  በተለይም በቆንዳላ ወረዳ በዚህ ሳምንት ብቻ በአንድ ቀበሌ ውስጥ አራት ህጻናት በወባ  ሕይወታቸው ማለፉንና ስርጭቱ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ነዋሪዎች አመልክተዋል። በቆንዳላ ወረዳ ወባን ለመከላከል የሚውለው አጎበር ለህብረተሰቡ ከተሰጠ 3 ዓመታትን እንዳስቆጠረ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ ወባ በሽታን በደረቅ አካባቢ ሳይቀር የምታሰራጨው ትንኝየምዕራብ ወለጋ ዞን የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ጫላ በበኩላቸው ፣በቤጊና ቆንዳላ ወረዳ ውስጥ፣ ወባ በሰው ላይ ጉዳት ማድረሱን አረጋግጠዋል፡፡ በቆንዳላ ወረዳ የወባ በሽታ ስርጭትን ለመቀነስ የኬሚካል ርጭት እንደሚከናወንም ተናግረዋል፡፡ በምዕራብ ወለጋ ዞን በቆንዳላ ወረዳ ገሚ ጋባ እና ካሴ በተባሉ ቀበሌዎች ውስጥ በዚህ ነሐሴ ወር ከ50 በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውን አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የወረዳው ጤና ተቋም ባለሞያዎችና ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡  

በአካባቢው ከቅርብ ጊዜ ወደህ ህጻናትን በፍጥነት እየየገለደ ያለውና ኮሌራ የሚመስል ምልክቶች ታይተዋል ሲሉ አንድ ጤና ጣቢያ ባለሙያዎች የተናገሩ ሲሆን የዞኑ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ  አቶ ሰለሞን ጫላ ሲመልሱ እስካሁን በተደረጉ የአካባቢ ጥናትና ክትትል  በዞናቸው የኮለራ በሽታ አለመገኘቱን ተናግረዋል፡
በቆንዳላ ወረዳ 2 የወንድማቸው ልጆች  ከትናንት በስቲያ እንደሞቱባቸውን የነገሩን አንድ የገሚ ጋባ ቀበሌ ነዋሪም የወባ በሽታ ስርጭት በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ተጽህኖ እያሳደረ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ምስል PongMoji/IMAGO

እንደ ባለሙያዎቹ ገለጻ ለበሽታው ማከሚያ የመድኃኒት አቅርቦት አነስተኛ መሆንና ለጉዳዩ ከዚህ ቀደም የነበረውን ያህል ትኩረት አለመሰጠቱ በሽታው በብዛት እንዲስፋፋ አድርገዋል፡፡ ከወባ በሽታ በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህናጻናትም በተለያዩ በሽታዎች እየሞቱ ነው ብለዋል፡፡ ማክሰኞ ዕለት በዚሁ በሽታ  3 ህጻናት በአንድ ጤና ጣቢያ ህይወታቸው ማለፉን ጠቁመዋል፡፡ በብዛት ከ10 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በበሽታው እየተጠቁ እንደሚገኙም አክለዋል፡፡‹‹ በዚህ አካባቢ ከአንድ ቤተሰብ ከሶስት አስከ 4 ሰዎችን ህይወታቸው እያለፈ ነው የሚገኘው፡፡ እንደ አጠቃላይ ህብረተሰቡ ለችግር ተጋልጠዋል፡፡ ህጻናትን የሚገድል ተላላፊ በሽታም አለ፡፡የወባ እና የደንጊ በሽታዎች ወረርሽኝ ስጋት በድሬዳዋ ትላንት ጠዋት በወባ በሽታ ህይወታቸው ያለፈ 3 ሰዎች ስርዓተ ቀብር ተፈጽመዋል፡፡ ይሄ ልዩ ትኩረት የሚሻ ነው‹‹ ብለዋል፡፡ በቆንዳላ ወረዳ 2 የወንድማቸው ልጆች  ከትናንት በስቲያ እንደሞቱባቸውን የነገሩን አንድ የገሚ ጋባ ቀበሌ ነዋሪም የወባ በሽታ ስርጭት በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ተጽህኖ እያሳደረ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ነዋሪው እንደሚሉትም የወባ በሽታ ስርጭት ከዚህ በዚህ መልኩ በከፍተኛ ደረጃ ታይቶ አይታወቅም፡፡

በምዕራብ ወለጋ ዞን በቆንዳላ ወረዳ ገሚ ጋባ እና ካሴ በተባሉ ቀበሌዎች ውስጥ በዚህ ነሐሴ ወር ከ50 በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውን አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የወረዳው ጤና ተቋም ባለሞያዎችና ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
 በምዕራብ ወለጋ ዞን በቆንዳላ ወረዳ ገሚ ጋባ እና ካሴ በተባሉ ቀበሌዎች ውስጥ በዚህ ነሐሴ ወር ከ50 በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውን አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የወረዳው ጤና ተቋም ባለሞያዎችና ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡  ምስል DW

‹‹ ከሐምሌ ወር ወዲህ ወባ በቀሌአችን  እስከ 30 የሚደርሱ ህጻናትግጭትና ወባ በወለጋ ህይወት አልፈዋል፡፡ ከወባ በተጨማሪ ህጻናትን ሆዳቸውን በማቁሰል የሚገድል በሽታ ተከስተዋል፡፡ በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅነዋል፡፡ መድሀኒትም እየተገኘ አይደለም፡፡‹‹ በምዕራብ ወለጋ ስር በሚገኙ ቆንዳላና ቤጊ ወረዳዎች የወባ ስርጭት መጨመሩን ሌላ አስተያየት የሰጡን የቤጊ ወረዳ ነዋሪም ነግረውናል፡፡ በቤጊ ወረዳም እንደዚሁ ከፍተኛ ጉዳት በህጸናት ላይ እየደረሰ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ ጤና ኬላዎች ውስጥ መድሀኒት የለም፡፡ ወደ ጤና ጣቢያ ቢንሄድም በቂ ህክምና እያገኘን አይደለም፡፡ ለወባ ድሮ ኬሚካል ይረጭ ነበር አጎበርም ይሰጥ ነበር አሁንም የለም፡፡ ከተሰጠን ረጅም ጊዜ ሆነዋል፡፡‹‹ የምዕራብ ወለጋ ዞን የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ጫላ  በቆንዳላ እና ቤጊ ወረዳዎች የወባ በሽታ ጉዳት ማድረሱን አረጋግጠዋል፡፡ የጉዳት መጠኑን በዝርዝር ባይገለጽሙም በየወሩ በሚደርሳቸው ዘገባ በሰው ህይወት ላይም ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡ በተለይም በቆንዳ ወረዳ የወባ በሽታ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑንና የጎላ  ጉዳት ከማድረሱ በፊት የኬሚካል ርጭት ለማከናወን በዞኑ ደረጃ ዝግጅት መደረጉሩንም አብራርተዋል፡፡

የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር ሰኔ 15/2015 ይፋ ባደረገው መረጃ በምዕራብ ወለጋ ቤጊ ወረዳ ብቻ 42 የሚደርሱ የጤና ተቋማት በደረሰባቸው ጉዳት እና ስርቆት በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት እንደማይሰጡ አመልክተዋል፡፡ 
የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር ሰኔ 15/2015 ይፋ ባደረገው መረጃ በምዕራብ ወለጋ ቤጊ ወረዳ ብቻ 42 የሚደርሱ የጤና ተቋማት በደረሰባቸው ጉዳት እና ስርቆት በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት እንደማይሰጡ አመልክተዋል፡፡ ምስል El Mundo/IMAGO

በአካባቢው ከቅርብ ጊዜ ወደህ ህጻናትን በፍጥነት እየየገለደ ያለውና ኮሌራ የሚመስል ምልክቶች ታይተዋል ሲሉ አንድ ጤና ጣቢያ ባለሙያዎች የተናገሩ ሲሆን የዞኑ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ  አቶ ሰለሞን ጫላ ሲመልሱ እስካሁን በተደረጉ የአካባቢ ጥናትና ክትትል  በዞናቸው የኮለራ በሽታ አለመገኘቱን ተናግረዋል፡፡  ‹‹ ወደ ቤጊና ቆንዳላ ወባ በሽታ የተለያዩ ጉዳቶችን ሲያደርስ ቆይተዋል፡፡ አሁንም ስርጭቱ  ጨምሮ እንዳለ ነው፡፡ በጤና ባለሞያ ደረጃ የተለያዩ መከላከል ስራዎችን እየሰራን ነው፡፡  በተለይም ቆንዳላ ወረዳ ላይ በሽታው ከወባ በሽታ ውጪም ሌላ ኬዝ አለ ተብሎ የሚነገር ወረ አለ ነገር ግን እስካሁን ሌላ የተገኘ በሽታ የለም፡፡ በየወሩ ከሚላኩልን ዘገባ በወባ በሽታ የሰዎች ህይወት እያለፈ እንደሚገኝ ደርሶናል፡፡ በቆንዳላ አሁን የኬሚካል ሪጭት ለመጀመር በዝግጅት ላይ ነን፡፡ ከዚህ ቀደም በጸጥታ ችግር በበርካታ ጤና ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ  ህብረተሰቡ በቂ ህክምና እያገኙ እንዳልሆነም ያነጋገርናቸው ነዋሪዎችም ተናግረዋል፡፡ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር ሰኔ 15/2015 ይፋ ባደረገው መረጃ በምዕራብ ወለጋ ቤጊ ወረዳ ብቻ 42 የሚደርሱ የጤና ተቋማት በደረሰባቸው ጉዳት እና ስርቆት በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት እንደማይሰጡ አመልክተዋል፡፡ 


ነጋሳ ደሳለኝ 


ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ