1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ላይ የአፋር ክልል አስተያየት

ሐሙስ፣ መጋቢት 16 2013

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአፋር እና የሶማሌ ክልሎች በሚዋሰኑባቸው ስምንት ቀበሌዎች "ሊከፈቱ የነበሩትን 30 የምርጫ ጣቢያዎች በአካባቢው እንዳይቋቋሙ" መወሰኑን ትናንት አስታውቋል። "የምርጫ ጣቢያዎቹ በሶማሌ ክልል በሚገኙ ቀበሌዎች ስም ይፋ ተደርገዋል" የሚል አቤቱታ ያቀረበውን የአፋር ክልል ስለውሳኔው ምን ይላል?

https://p.dw.com/p/3r8jI
Logo | National Election Board of Ethiopia
ምስል National Election Board of Ethiopia

በምርጫ ቦርድ ውሳኔ ላይ የአፋር ክልል አስተያየት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአፋር እና የሶማሌ ክልሎች በሚዋሰኑባቸው ስምንት ቀበሌዎች "ሊከፈቱ የነበሩትን 30 የምርጫ ጣቢያዎች በአካባቢው እንዳይቋቋሙ" መወሰኑን ትናንት አስታውቋል። 
"ቦርዱ በ2007 ዓ.ም የተጠቀመበትን የመረጃ ዝርዝር ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ ቢጠቀምም፣ የምርጫ ጣቢያዎች የአስተዳደር ወሰኖችን የሚወስኑ መገለጫዎች ባይሆኑም ቦርዱ ምርጫ በምንም መልኩ የሰላም መደፍረስ ምክንያት እንዳይሆን በማሰብ" ከውሳኔው እንደደረሰ የትናንትናው መግለጫ ይጠቁማል። 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ "በአካባቢው የሚኖሩ እና የመራጮች ምዝገባ እና የድምጽ መስጠት ሂደት ውስጥ የሚሳተፉ ዜጎች በአቅራቢያቸው ባለ ሌላ ቀበሌ መመዝገብ እና ድምጻቸውን መስጠት" ይችላሉ ብሏል። ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር "የምርጫ ጣቢያዎቹ በሶማሌ ክልል በሚገኙ ቀበሌዎች ስም ይፋ ተደርገዋል" የሚል አቤቱታ ያቀረበውን የአፋር ክልል ባለሥልጣናት ምላሽ በትናንትናው ውሳኔ ላይ ጠይቋል።

ዮሐንስ ገብረእግዚዓብሔር
ነጋሽ መሐመድ