1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በመተከል ዞን የቀጠለው የነዋሪዎች ቅሬታ

ሰኞ፣ መጋቢት 27 2013

ሰላም ለማስፈን በየወረዳው የተለያዩ የእርቅ ጉባኤዎች መካሄዳቸውን የግልገል በለስ ነዋሪዎች ቢገልጹም ወንጀሎች ለሕግ ባለመቅረባቸው በየቦታ በመንቀሳቀስ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እያደረሱ እደሚገኙ ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/3rbMt
Karte Äthiopien Metekel EN

«የጸጥታው ችግር በመንግሥት እንዲፈታ ጠይቀዋል»

የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች በሰው እና ንብረት አሁንም ጥቃቶች እየደረሱ መሆንን ነዋሪዎች አስታውቀዋል።  በአካባቢው የሚስተዋለውን የጸጥታ ችግር መንግሥት በዘላቂነት  እንዲፈታም ጠይቀዋል። በድባጢ ወረዳም ሰሙኑን በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎች የተናገሩ ሲሆን የመጓጓዣ አገልግሎት  ባለመኖሩ መቸገራውንም አክለዋል። ከነዋሪው ለተነሱት ቅሬታዎች ከአካባቢው አስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር ወይም ኮማንድ ፖስት ስልክ ባለማንሳታቸው መረጃ ለማግኘት አልተቻለም።

ነጋሳ ደሳለኝ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ