1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሆሮ ጎደሩ ወለጋ ዞን ስድስት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ

ነጋሳ ደሳለኝ
ሰኞ፣ መስከረም 20 2017

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ የጸጥታ ሀይሎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ያለፈው ቅዳሜ በታጣቂዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ በወረዳው አጋምሳ ከሚባል ከተማ ወደ አጎራባች ኪረሙ ወረዳ በመጓዝ ላይ የነበረ አንድ ግለሰብም በታጠቁ ሐይሎች ታግቶ በሚሊዩን የሚቆጠር ገንዘብ በአጋቾች እንደተጠየቀበት ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4lEjY
ነቀምት ከተማ
በኦሮሚያ ክልል የነቀምት ከተማምስል Negasa Desalegn/DW

በሆሮ ጎደሩ ወለጋ ዞን ስድስት ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ የጸጥታ ሀይሎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጸጥታ ሁኔታው ተሻሽሏል ተብሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው የተመለሱባት አሙሩ ወረዳ ቅዳሜ ዕለት በሸማቂዎች እና በወረዳው ሚሊሻዎች መካከል ወልቂጤ በሚባል ቦታ ለረጅም ሰዓት የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል፡፡

በወረዳው አጋምሳ ከሚባል ከተማ ወደ አጎራባች ኪረሙ የተባለ ወረዳ በመጓዝ የነበረ አንድ ግለሰብም በታጠቁ ሐይሎች ታግቶ በሚሊዩን የሚቆጠር ገንዘብ በአጋቾች እንደተጠየቀበት ነዋሪዎቹ ጨምረው ገልጸዋል።

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ የጸጥታ ሀይሎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጸጥታ ሁኔታው ተሻሽሏል ተብሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቤታቸው የተመለሱባት አሙሩ ወረዳ ቅዳሜ በሸማቂዎች እና የወረዳው ሚሊሻዎች መካከል ወልቂጤ በሚባል ቦታ ለረጅም ሰዓት የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡ በወረዳው አጋምሳ ከሚባል ከተማ ወደ አጎራባች ኪረሙ የተባለ ወረዳ ሲጓዝ  የነበረ አንድ ግለሰብ በታጠቁ ሐይሎች ታግቶ በሚሊዩን የሚቆጠር ገንዘብ በአጋቾች እንደተጠየቀበት ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል፡፡

ከሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አስተዳዳር ዋና መቀመጫ ከሆነው ሻምቡ ከተማ በ96 ኪ.ሜ ርቀት ገደማ ላይ የሚትገኘዋ አሙሩ ወረዳ ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ በሸማቂዎችና ሚሊሻዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት የሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ በወረዳው በጥበቃ ላይ የነበሩ የሚሊሻ አባላት እና ሸማቆዎች መከካል ለሰዓታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የአካባቢ ነዋሪ ጠቁመዋል፡፡

ኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጎደሩ ወለጋ
ኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጎደሩ ወለጋ ምስል Negassa Dessalegn/DW

‹‹ የሚሊሻ ሐይል እና ሸማቂዎች ተጋጭተው በርካታ ሰዎች ተጎተዋል፡፡ በአሙሩ ወረዳ ወልቂጠ በተባለው ቦታ ነው ግጭቱ የተከሰተው፡፡ ባጠቀላይ ጸጥታ ሀይሎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ህይወት አልፈዋል፡፡ በተጨማሪም በአጎራባች ኪረሙ ወረዳ ሀሮ የተባለ ቦታ ባለፈው ቅዳሜ አንድ ባጃጅ ሹፈር ታግተው 3 ሚሊዩን ብር ተጠይቆበታል፡፡‹‹

በአሙሩ ቅዳሜ በተከሰተውግጭት የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን እንደሚያውቁ የተናገሩት ሌላው የአካባቢው ነዋሪም ታጣቂዎች ሀሮ ከሚባል ስፍራ እና ከአባይ ወንዝ በመሻገር ጥቃት እንደሚፈጽሙ ተናግረዋል፡፡ በወረዳው በተለያዩ ስም የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ከዚህ ቀደምም ተደጋጋሚ ጥቃቶችን መፈጸማቸውን ገልጸዋል፡፡

‹‹ ሚሊሻና ጫካ የሚኖሩ ታጣቂዎች ናቸው የተጋጩት፡፡ ብዙ ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋም ደርሷል፡፡ ከሸማቂዎች አንድ ሰው ሞቷል፡፡

 የኦሮሚያ ክልል ገጠራማ አካባቢ
በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል ገጠራማ አካባቢ ምስል Seyoum Getu/DW

በሆሮ ጉሩ ወለጋ አሙሩ ወረዳ በተደጋጋሚ ለሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮችን በዘለቂነት ለመፍታት ለምን አልቻተለም ብለን የጠቅናቸው የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ሀላፊ አቶ አበበ ነጋሽ ወረዳው አባይ ወንዝና ኪረሙ ወረዳ ሀሮ የተባሉ በርካታየታጠቁ ሐይሎች የሚገኙበት ስፍራዎችን የሚያወስን በመሆኑ ስራውን ፈታኝ እንዳደረገው ጠቁመዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የወረዳው ሚሊሻ አካባቢውን እየጠበቁ እንደሚገኙ ገልጸው አብዛኛው በወረዳው የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮች አጎራባች ቦታዎች የሚነሱ እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡ ባለፈው ቅዳሜ በወረዳው በጸጥታ ሐይሎችና ሸማቂዎች መካከል በተከሰተው ግጭትም የሰዎች ህይወት ማለፉን የገለጹ ሲሆን በግጭቱ የደረሰውን የተጉዳት መጠን መግለጽ አልፈለጉም፡፡

‹‹ የወረዳው ሠላም እንጠቃላይ ተሻሽሏል፡፡ አልፎ አልፎ የሽፍታ ባህሪ በመሆኑ ችግሮች ይፈጠራሉ። በሰዎች ላይ ጉዳት ያደርሳሉ፡፡መቶ በመቶ ሰላም ሰፍኗል የሚልም ድምዳሜ ላይ አልደረሰንም፡፡ ሽፍቶች በመንገድ ላይ ሰዎችን ማገትና የማስራራት ስራ ይሰራሉ፡፡ አሙሩ በአባይ በኩል ከአማራ ክልልና በአንደ በኩል ደግሞ ኪረሙ ወረዳ ጋር ይዋሰናል፡፡ በኪረሙ ሆሮ እና ባግን ከሚባሉ ቦታዎች ሸማቂዎች በመኖራቸው አሁንም ስጋት አለ ብሏል፡፡‹‹

አሙሩ ወረዳ ከሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን ወረዳዎች በተደጋጋሚ የታጣቂዎች ጥቃት የደረሰባት ወረዳ ስትሆን ባለፉት አምስት ወራት የአካባቢው ሰላም መሻሻሉንና የተፈናቀሉ ዜጎች ወደየቀያቸው መመለሳቸው ተዘግበዋል፡፡

 

ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።


ነጋሳ ደሳለኝ
አዜብ ታደሰ
ፀሐይ ጫኔ