1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካየመካከለኛው ምሥራቅ

በሃማስ የታገቱ ጥቂት እስራኤላዉያን ተለቀቁ

ዓርብ፣ ኅዳር 14 2016

በእስራኤልና በሃማስ መካከል የታጋች እና እስረኛ ልዉዉጥ ተካሄደ ነዉ። የዓለም አይኖች ትኩረታቸዉን መካከለኛዉ ምስራቅ ላይ አድርገዋል ። ጋዛ ዛሬ ወደ 60 ሰብዓዊ እርዳታን የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎችን አግኝታለች። ከ 13 እስራኤላዉያን ታጋቾች በተጨማሪ በሃማስ እጅ የነበሩ 10 ታይላንዶችም ተለቀዋል።

https://p.dw.com/p/4ZQVU
በሃማስ የታገቱ ጥቂት እስራኤላዉያን ተለቀቁ
በሃማስ የታገቱ ጥቂት እስራኤላዉያን ተለቀቁ ምስል MOHAMMED ABED/AFP

ለአራት ቀናት የሚቆየውንም የተኩስ አቁም ተከትሎ በእስራኤልና በሃማስ መካከል የታጋች እና እስረኛ ልዉዉጥ እየተካሄደ ነዉ። እርዳታ ወደ ጋዛ ሰርጥ መግባት መጀመሩም ተገልጿል። በስምምነቱ መሠረት ዛሬ ህጻናትን ጨምሮ 13 የእስራኤል ታጋቾች በግብፅ በኩል ለዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ድርጅት መሰጠታቸዉን የእስራኤል ቴሌቭዥን ዘግባል። በግብፅ ራፋህ የድንበር በኩል የእስራኤል ወታደራዊ ኃይሎች በሄሊኮፕተር ተቀብለው አስፈላጊውን የማንነት ማረጋገጫ ያደርጋሉ፤ በመቀጠልም የሕክምና ምርመራ ከተደረገላቸዉ በኃላ  ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንደሚገኛኑ ተገልጿል። ይለቀቃሉ ከተባሉ 13 ታጋቾች በተጨማሪ ሌላ ታግተዉ የነበሩ 10 የታይላንድ ዜጎችም መለቀቃቸዉ ተመልክቷል። እስካሁን የተለቀቁት የእስራኤል ኃጋቾች ማንነት አልተገለፀም። በሚቀጥሉት ደቂቃዎc እና ሰዓታት ይፋ እንደሚነገር ይጠበቃል። እስራኤል በእስር ከያዘቻቸው በሺዎች ከሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን መካከል  የተወሰኑት ዛሬ እንደሚለቀቁ ይጠበቃል። ከእስራኤል በኩል የሚለቀቁት ፍልስጤማዉያን፤ መካከል ታዳጊ ህጻናት እና ወጣቶች እንደሆኑ ተገልጿል። በእስራኤል ታስረዉ የነበሩት እነዚህ ፍልስጤማዉያን  በእስራኤል ፀጥታ ሃይላት ላይ ድንጋይ በመወርወር ወይም የኃይል ጥቃት በማድረስ ተይዘዉ የነበሩ ናቸዉ፤  ተብሏል። እስራኤል እና ሃማስ የተለዋወጥዋቸዉ እስረኞችም ሆኖ ታጎቾች እስካሁን በይፋ አልወጡም የዓለም አይኖች ትኩረታቸዉን መካከለኛዉ ምስራቅ ላይ እንዳደረጉ ነዉ።

በሃማስ የታገቱ እስራኤላዉያን ቤተሰቦች
በሃማስ የታገቱ እስራኤላዉያን ቤተሰቦችምስል Ariel Schalit/AP/picture alliance

በሌላ በኩል እስራኤል እና ሐማስ መካከል የሚካሄደው ጦርነት ለቀናቶች ለማቆም እና ታጋቾችን ለመልቀቅ ከስምምነት መድረሱን ተከትሎ  ወደ ጋዛ የሚገባው የሰብዓዊ እርዳታ መጠን እየጨመረ መሆኑ ተዘግቧል። ስምምነቱ ተፈጻሚ ከሆነበት ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ቢያንስ 60  የሰብዓዊ ቁሳቁስ እና ምግብ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ጋዛ መግባታቸዉ ተነግሯል። ግብጽ በበኩልዋ በየቀኑ 130 ሺህ ሊትር ነዳጅ ወደ ጋዛ እንደሚገባ አስታዉቃለች። በሚቀጥሉት አራት ቀናት ወደ ጋዛ 200 የሚጠጉ የሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ጋዛ እንደሚገቡ ይጠበቃል። ይሁንና ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚሆነዉ እርዳታ ጠባቂ ፍልስጤማዉያን በቂ መሆኑ አጠራጣሪ ተብሏል።   
የእስራኤል ጦር ሰራዊት ቃል አቀባይ  ፍልስጤማዉያን ወደ ሰሜናዊ ጋዛ እንዳይመለሱ ሲል ጥሪ ዛሬ አደረገ። እንደ ጦር ሰራዊቱ ቃል አቀባይ የተኩስ አቁም  ስምምነት ለቀናቶች ተደረገ እንጂ ጦርነቱ አልቆመም፤ ወደ ሰሜናዊ ጋዛ እንዳትመለሱ ሲል ለፍልስጤማዉያን ጥሪ አቅርቧል። ይሁንና ተጨማሪ ታጋቾች የሚለቀቁ ከሆነ የተኩስ አቁም ቀናቶች ከአራት ቀናቱ ሊጨምር እንደሚችል ተመልክቷል።

በሃማስ የታገቱ እስራኤላዉያን ቤተሰቦች
በሃማስ የታገቱ እስራኤላዉያን ቤተሰቦችምስል Ariel Schalit/AP/picture alliance

 
አዜብ ታደሰ 

ዮኃንስ ገብረግዚአብሔር