1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሶማሌ ክልል ሼቤሌ ዞን የጎርፍ መጥለቅለቅ ብርቱ ጉዳት

ረቡዕ፣ ኅዳር 19 2016

በሶማሌ ክልል 33 ወረዳዎች በ140 ቀበሌዎች ለ28 ሰዎች ሞት ሰበብ የሆነው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ በሺህዎች የሚቆጠሩትን ማፈናቀሉ ተገለጸ ። ጎርፉ በእንስሳት ፣ በእርሻ እና መሰረተ ልማቶች ላይም ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል ።

https://p.dw.com/p/4ZZnC

በሶማሌ ክልል 33 ወረዳዎች በ140 ቀበሌዎች ለ28 ሰዎች ሞት ሰበብ የሆነው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ በሺህዎች የሚቆጠሩትን ማፈናቀሉ ተገለጸ ። ጎርፉ በእንስሳት ፣ በእርሻ እና መሰረተ ልማቶች ላይም ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል ። በጎርፍ እና የወንዝ ሙላት ሳቢያ ብርቱ ጉዳት ከገጠማቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው የሼቤሌ ዞን ከሃምሳ ሰባት ሺህ በላይ አባወራዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የዞኑ አስተዳደር ለዶይቼ ቬለ አስታውቋል ።

የቪዲዮ ዘገባ፦ መሳይ ተክሉ ዶይቸ ቬለ (DW) ከአዲስ አበባ