1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሕዝብ አስተያየት

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 9 2015

በአማራ ክልል የተፈጠረውን ወቅታዊ የፀጥታ መደፍረስን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት በትናትናው ዕለት አደጋውን ለመቀልበስ ይረዳኛል ያለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጸድቋል ።

https://p.dw.com/p/4VCmN
የአዲስ አበባ ከተማ ገፅታ፦ ፎቶ ከማኅደር
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ነዋሪዎች የተለያዩ ሐሳቦችን ሰንዝረዋል ። የአዲስ አበባ ከተማ ገፅታ፦ ፎቶ ከማኅደር ምስል Seyoum Getu/DW

አዋጁ ድጋፍም ተቃውሞም ተስተናግዶበታል

በአማራ ክልል የተፈጠረውን ወቅታዊ የፀጥታ መደፍረስን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በትናትናው እለት አደጋውን ለመቀልበስ ይረዳኛል ያለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጸድቋል ። ይሁንና ሕጉ በተወካዮች ምክር ቤቱም ብርቱ ሙግት ገጥሞታል ።

ከአሁናዊ የክልሉ ሁኔታ እና ዘላቂ እልባቱ ጋር በተያያዘም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አስፈላጊነት ላይ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው ። «ህዝብ አንደ ሕዝብ ተነሳ» ጥያቄውም መመለስ ይገባዋል እንጂ አስኳይ ጊዜ አዋጅ አያስፈልግም ሲሉ አስተያየት የሰጡ አሉ ። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ደግሞ፦ «ሕግ እና ስርዓት ማስከበር ሳይቻል ሀገርን ለመታደግ የሚታወጅ አዋጅ ስለሆነ» ሀገርን ለመታደግ አስፈላጊ ነው የሚል አተያየት ሰጥተዋል ።

ሌላ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው «የኢፌዴሪ ሕገመንግሥትን» ጣቅሰው አዋጁ ተገቢ ነውብለዋል ። «በሰላማዊ ሰልፍም ሆነ» በሌሎች መንገዶች ጥያቄዎችን ብጠይቅ መልስ አላገኘሁም ያለ ማኅበረሰብ «ብቸኛው አማራች ሊሆን የሚችለው ነፍጥ አንስቶ ከመንግስት ጋር መዋጋት ነው የሚል ደግሞ ይሄ ሌላ ዕይታ ሊሆን ይችላል» ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ገፅታ፦ ፎቶ ከማኅደር
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ነዋሪዎች የተለያዩ ሐሳቦችን ሰንዝረዋል ። ከአሁናዊ የክልሉ ሁኔታ እና ዘላቂ እልባቱ ጋር በተያያዘም አስተያየቶች እየተሰጡ ነው ። የአዲስ አበባ ከተማ ገፅታ፦ ፎቶ ከማኅደር ምስል Seyoum Getu/DW

ኢሰመኮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአማራ ክልል ብቻ እንዲወሰን ለመንግስት ጥሪ አቀረበ

ዘጋቢችን ሥዩም ጌቱ ከተወሰኑ የተለያዩ አስተያየቶች ከሰነዘሩ የማኅበረሰብ አካላት ሐሳባቸውን አጠይቋል፡ ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን የተቃወሙም የደገፉም አሉበት ።

ሥዩም ጌቱ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ

የአዲስ አበባ ከተማ ገፅታ፦ ፎቶ ከማኅደር
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ነዋሪዎች የተለያዩ ሐሳቦችን ሰንዝረዋል ። ከአሁናዊ የክልሉ ሁኔታ እና ዘላቂ እልባቱ ጋር በተያያዘም አስተያየቶች እየተሰጡ ነው ። የአዲስ አበባ ከተማ ገፅታ፦ ፎቶ ከማኅደር ምስል Seyoum Getu/DW