1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሳይጀመር የከሸፈው የሰላም ድርድር

ሐሙስ፣ ጥቅምት 3 2015

ጦርነቱ ከትግራይ አልፎ እስከመሀል አገርና አፋር ክልል ተስፋፍቶ ያደረሰውና እያደርሰ ያለው ጉዳት ከበርካታ አስርት አመታት ወዲህ በአገሪቱ ደርሶ የማያውቅ እንደሆነ ነው የሚታመነው። የአፍሪካ ህብረት፣ የአውሮፓ ህብረትና አሜሪካ ልዩ ለዑካኖችን ለአካባቢው በመመደብ ጭምር ጦርነቱ እንዲቆም ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ተደጋግሞ ይገለጻል።

https://p.dw.com/p/4I9X5
Kombobild | Uhuru Kenyatta, Olusegun Obasanjo, Phumzile Mlambo-Ngcuka
በኢትዮጵያ ሊደረግ ከታቀደው ድርድር ጋር ስማቸው ጎልቶ የሚነሳ ጉምቱ ፖለቲከኞች

ታሳቢ ምክንያቶች

ጦርነቱ ከትግራይ አልፎ እስከመሀል አገርና አፋር ክልል ተስፋፍቶ ያደረሰውና እያደርሰ ያለው ጉዳት ከበርካታ አስርት አመታት  ወዲህ በአገሪቱ ደርሶ የማያውቅ እንደሆነ ነው የሚታመነው። የአፍሪካ ህብረት፣ የአውሮፓ ህብረትና አሜሪካ ልዩ ለዑካኖችን ለአካባቢው በመመደብ ጭምር ጦርነቱ እንዲቆም ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ተደጋግሞ ይገለጻል። በተለይ የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባስንጆ ደጋግመው ወደ መቀሌ በመሄድ ጭምር ሁለቱ ወገኖች ተገናኝተው በመወያየት ጦርነቱን አቁመው ሰላም እንዲፈጥሩ ለማድረግ ሲጥሩ ቆይተዋል። ከብዙ ግዜ ጥረት በኋላም የአፍሪካ ህብረት ከዋናው የሰላም አደራዳሪ ኦባስንጆ በተጨማሪ የቀድሞውን የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡህሩ ኬንይታንና የቀድሞዋን የደቡብ አፍርካ ምክትል ፕሬሽዳንት  ፉሙዚሌ ምልላምቦ ንጉካን በተጨማሪ አደራዳሪነት  በመሰየም ባለፈው ቅድሜ ሁለቱን ወገኖች በደቡብ ፍርክ ፕሪቶሪያ ለማገናኘት ቀጠሮ ተይዞ ነበር። ሆኖም ግን ከቀጠሮው ቀን አንድ ቀን በፊት፤ በሎጂስቲክስ ችግር ምክንያት የስብሰባው ግዜ መራዘሙ ተነግሯል። ቀደም ብሎም ኬንያታ በተደራራቢ ፕሮግራም ምክንያት በዕለቱ እንደማይገኙና ስለድርድሩ ይዘትና ሂደትም ማብራሪያ እንደሚፈልጉ መጠየቃቸው ተገልጾ ነበር።  በዚህም ምክንያትም የተጠበቀው የሰላም ንግግር ሳይካሄድ ቀርቷል፤ ጦርነቱም ቀጥሏል።  

ዶቼ ቬለ ይህን ሳይጀመር የተቋረጠውን የሰላም ንግግር አስመልክቶ፤ ከዓለም አቀፉ የግጭቶች ተከታታይ ድርጅት (ክራይሥሥ ግሩፕ)፤ የኢትዮጵያ ተከታታይና ተመራማሪ ከሆኑት ዊሊይም ዳቪሰን ጋር በስልክ አጭር ቆይታ አድርጓል።ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ እና የኢትዮጵያው የድርድር ተስፋ

 ይህን ደም አፋሳሺ ጦርነት ለማስቆም የመጀመሪያ ሊሆን የሚችለው  የሰላም ንግግር  ቀን ከተቆረጠለት በኋላ በሎጂስቲክስ ችግር ተላልፏል መባሉ በቂ ምክንያት ነው ወይ? ወይንስ ሊሎች ያልተገለጹ ምክንያቶች አሉ?

የናይጀሪያ ፕሬዝደንት ኦሊሴንጎን ኦባሳንጆ ከህወሓት ባለስልጣናት ጋር ሲመክሩ
የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ ልዑክ የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዝደንት ኦሊሴንጎን ኦባሳንጆ መቀሌ በተገኙበት ወቅትምስል Privat

“የአፍሪካ ህብረት የግብዣ ደብዳቤ ዘግይቶ የተላከና ዝርዝር ሁኒታዎችንም የማይጠቅስ እንደነበር የሚታወቅ ነው። እንደትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት የመሠሉ የሚመለክታቸው ቡድኖች ብቻ ሳይሆኑ ተጨማሪ አደራዳሪው ዑሁሩ ኬንየታም ስለስብሰባው በቂ መረጃ የነበራቸው አይመስልም። በዚህም ምክንያት ነው በርካታ ጉድዮች ላይ ማብራሪያዎችን የጠይቁት። በተጨማሪም በድርድሩ ሂደትና አያያዝ ላይም ግልጽ ያልሆኑ በርካታ ጉዳዮች አሉ። የትግራይ አመራሮች የኦባስንጆን መሪ አደራዳሪነት የመቀበላቸው ሁኔታ ግልጽ አይደለም። በትግራይ በኩል የአሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች በድርድሩ ሚና እንዲኖራቸው ፍላጎት ያለ ቢሆንም፤ ይህ ግን በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ምን ያህል ተቀባይነት እንዳለው ግልጽ አይደለም።»  በማለት ለስብሰባው መራዘም ዋና ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ ያሏቸውን ዘርዝረዋል። ሚስተር ዊሊይም አክለውም «በትግራይ ሀይሎች በኩል  ማንኛውም የሰላም ንግግር፤ የትግራይን ከበባ የሚያስወግድና አገልግሎቶችን የሚያስጀምር፤ ያልተገደበ የርዳታ አቅርቦት የሚያረጋግጥና የኤርትራ ሠራዊት እንዲወጣ እንዲሁም የአማራ ሀይሎች በምዕራብ ትግራይ ያላቸው ቆይታ እንዲያበቃ የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች እንዳሉ የሚታወቅ በመሆኑ፤ በሰላም ንግግሩ እነዚህ ሁሉ ጉዳዮች እንዴት እንደሚያዙ አይታወቅም» በማለት በሁለቱ ወገኖች መካከል አሁንም ከፍተኛ ልዩነቶች እንዳሉና  ለሰላሙ ሂደት መደናቀፍም እነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ሊጠቀሱ እንደሚችሉ አንስተዋል።ኢትዮጵያ የድርድር ፖለቲካ የናፈቃት ሐገር

International Crisis Group
የዓለም አቀፉ የቀውስ ተቀከታታይ ክራይስስ ግሩፕ መለያምስል International Crisis Group

ሚስተር ዊሊያምን ከዚህ በኋላስ ለሰላም ያለው ተስፋ ምንድን ነው ምንስ ሊደረግ ይገባዋል? በማለት ለቀረበላቸው ጥይቄ፤ «ሁኔታው አስቸጋሪ መሆኑንና በጦርነቱ አሁንም በርክቶች እየሞቱና ትግራይም በከበባ ውስጥ እንዳለች» የቀጠለች መሆኑን አውስተው፤ ሁኔታው ለትግራይ ብቻ ሳይሆን ለአማራና አፋር ማኅበረሰቦችም አስቸጋሪ መሆኑን ገልጸዋል ። ከዚህ ችግር ለመውጣትና ለሰላም ዕድል ለመስጠት «በዓለም አቀፉ ማኋብረሰብ በኩል የተቀናጀ የዲፕላማሲ ጥረት ያስፈልጋል። ችግሮችን በመለየትና  በውጭ ተዋንያን መካከል ያለውን ልዩነትም ለይቶ በማውጣትና በመግባባት  ሁለቱ ወገኖች በሰላሙ ንግግር እንዲክፈሉ የሚጋብዝ የተሻሻለ የግብዣ ደብዳቤ መላክ ይኖርበታል» በማለት ገልጸዋል።

ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ