ማኅበረሰቡን የፈተነዉ የኑሮ ዉድነት
ሰኞ፣ የካቲት 8 2013ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ያስከተለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት የከተሜውን ሕይወት እየፈተነው ይገኛል። መንግሥት አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እያደረገ ቢሆንም መቋሚያ ያጣው የሸቀጦች የዋጋ ማሻቀብ ከሥራ አጥነት ፣ ከወጪ ንግድ መቀዛቀዝ፣ ከውጪ ምንዛሪ እጥረት ፣ ከብር የመግዛት አቅም መዳከም ጋር ተደማምሮ አናኗርን ፈተና ውስጥ እየጣለው ይገኛል። የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች በተለይ ሰሞነኛው የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ያስከተለው የዋጋ ጭማሪ ሌላ ራስ ምታት መደቀኑን አበክረው እየተናገሩ ሲሆን መንግስት በበኩሉ ስለዚህ ጉዳይ ያለው ነገር የለም። ኢትዮጵያ የገባችበት የፖለቲካ ምስቅልቅል ለኑሮ ውድነት መባባሱ ተጨማሪ ችግር መሆኑም እዚህም እዚያም ይደመጣል።
ሰለሞን ሙጬ