1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«በባህርዳርና በጎንደር በረራ ነገ በረራ ይጀመራል»

ሐሙስ፣ ነሐሴ 4 2015

መከላከያ ሠራዊት በከተማው ውስጥ እንደሌለ የገለፁ አንድ የደብረታቦር ከተማ ነዋሪ ፋኖዎቹ የመንግሥት ሠራተኞች ሥራቸውን እንዱሰሩ እያዘዙ መሆኑን፣ ማን ይሰራል ፣ ማን አይሰራም የሚለውንም እየመዘገቡ መሆኑን መስማታቸውን ገልፀዋል። በአካባቢው የነበረ የመከላከያ ሠራዊት ወደ ጎንደር መስመር አዲስ ዘመን አካባቢ መሄዱንም ገልፀዋል።

https://p.dw.com/p/4Uxdy
Äthiopien Gondar
የጎንደር ከተማምስል Alemenew Mekonnen/DW

የኢትዮጵያ አየር መንገድ  ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች በጊዜያዊነት አቋርጦት የነበረውን መደበኛ በረራ ነገ እንደሚጀምር አስታውቋል።። አየር መንገዱ ትናንት አውጥቶት በነበረው መግለጫ ዛሬ ረቡዕ፣ ሐሙስ እና ዓርብ ወደ ደሴ (ኮምቦልቻ)፣ ጎንደር፣ ላሊበላ እና ባህር ዳር ከተሞች የሚደረጉ በረራዎች ተሰርዘዋል ብሎ ነበር። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነገ በረራ እጀምርበታለው ባለው የጎንደር ከተማ ዛሬ  ምንም የተኩስ ድምፅ እንዳልነበር ሆኖም ግን ከተማው ከእንቅስቃሴ እንደተገደበ መሆኑን  ነዋሪዎች ገልፀዋል። አማራ ክልል በተፈጠረው ግጭት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል አምቡላንሶች ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን ገልጿል። ተቋሙ በሥራው ላይ ስለተፈጠረው መስተጓጎል እና ስለደረሰው የሰብዓዊ ቀውስ በነገው እለት ለመገናኛ ብዘኃን መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቋል። የአማራ ክልል እንዴት ዋለ?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ብርቱ ውጊያ ሲደረግባቸው ወደ ሰነበቱት ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች ነገ መደበኛ በረራ እንደሚጀምር ሲያስታውቅ አገልግሎቱን ለምን አቋርጦ እንደነበር በግልጽ ያለው ነገር የለም። ወደ ኮምቦልቻ እና ላሊበላ መደበኛ በረራውን መቼ እንደሚጀምርም አልገለፀም። መከላከያ ሠራዊት በከተማው ውስጥ እንደሌለ የገለፁ አንድ  የደብረታቦር ከተማ ነዋሪ ፋኖዎቹ የመንግሥት ሠራተኞች ሥራቸውን እንዱሰሩ እያዘዙ መሆኑን፣ ማን ይሰራል ፣ ማን አይሰራም የሚለውንም እየመዘገቡ መሆኑን መስማታቸውን ገልፀዋል። በአካባቢው የነበረ የመከላከያ ሠራዊት ወደ ጎንደር መስመር አዲስ ዘመን አካባቢ መሄዱንም ገልፀዋል። አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን ባወጣው መግለጫ የአማራ ክልልን መንግሥት "ቀርጠኝነት እና ብቃት የሌለው" በሚል ከሷል። በክልሉ ለተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ፣ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ መንግሥት ኃላፊነት ወስዶ ሕዝቡን ይቅርታ እንዲጠይቅ በመግለጫው ያሰፈረው ፓርቲው ይህን ያህል ብሎ ባይጠቅስም ሰዎች መመታቸውን፣ ለአካል ጉዳትና ለሌሎች ችግሮች መዳረጋቸውን ገልጿል።የአማራ ክልል ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታና ኮማንድ ፖስት
በክልሉ ዋና ዋና ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች ህክምና እያገኙ ያሉ የግጭቱ ሰለባዎች ስለመኖር አለመኖራቸው ለማጣራት ያደረግሁት ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
በጎንደር ከተማ ከትናንት አመሻሽ ጀምሮ መብራት መጥፋቱን የገለፁ አንድ ነዋሪ ግን ሰሞኑን በነበረው ውጊያ ንፁሃን ዜጎች ለጉዳት ስለመዳረጋቸው ገልፀዋል።ግጭቱ በከተማዋ በ2008 እና 2009 ዓ.ም ከነበረው ተመሳሳይ ችግር የከፋ እና ብዘ ጉዳት ያስከተለ መሆኑንም ተናግረዋል።  "በቅርቡ በአማራ ክልል በተቀሰቀሰዉ ግጭት ምክንያት ከፍተኛ ሰብኣዊ ጉዳቶች እየደረሱ ይገኛሉ" ያለው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር "በግጭቱ ሰለባ የሆኑ ወገኖችን ለመርዳትና በክልሉ ከዚህ የከፋ ቀዉስ ከመከሰቱ በፊት አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፎችና ምላሾችን ለመስጠት እንቅስቃሴ ጀምሯል" ሲል አስታውቋል።በክልሉ ለማድረግ የታሰበውን የሰብዓዊ ድጋግ እና ምላሽ በተመልከተም ነገ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቋል።
ሰሎሞን ሙጬ 
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ

Äthiopien Gondar | Bilder zur aktuellen Sicherheitslage
ጎንደር ከተማምስል Nebiyu Sirak/DW
Ethiopian Airlines
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንምስል Solomon Muche/DW