1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መቐለ በሺህዎች የሚቆጠሩ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ረቡዕ፣ ጥር 15 2016

በሺዎች የሚቆጠሩ በመቐለ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያ ቀዬያችን መልሱን ሲሉ ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ።ልፈኛ ተፈናቃዮቹ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እና የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት በፕሪቶሪያ ያደረጉትን ስምምነት እየተገበሩ አይደለም በማለት ቅሬታቸውን ገልጠዋል ።

https://p.dw.com/p/4bdSF
ተቃውሞ መቐለ
የተቃውሞ ሰልፈኞች በመቐለምስል Million Haileselassie/DW

ሰልፈኞቹ ወደ ቀዬያችን መልሱን ብለዋል

በሺዎች የሚቆጠሩ በመቐለ ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ መኖሪያ ቀዬያችን መልሱን ሲሉ ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ። ሰልፈኛ ተፈናቃዮቹ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እና የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት በፕሪቶሪያ ያደረጉትን ስምምነት እየተገበሩ አይደለም በማለት ቅሬታቸውን ገልጠዋል ። ዓለም አቀፍ ለጋሾችም የርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል። ተፈናቃዮች በአስከፊ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን አስተዳደራቸው እንደሚገነዘብ የተናገሩት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ «ፌደራል መንግሰት ሥራውን» አልሠራም ሲሉ ወቅሰዋል ። «በእኛ በኩልም የሚጠበቅብን ጥረት ማድረግ ሲገባን ባለማድረጋችን» በማለት ችግሩ ወደከፋ ደረጃ ለመድረሱ በይፋ «ይቅርታ» ጠይቀዋል። 

መነሻቸውን በመቐለ የሚገኙ የተለያዩ መጠልያ ጣብያዎች እና ሌሎች አካባቢዎች ያደረጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች፥ በከተማዋ «ማርታ አደባባይ» ተሰባስበው የተቃውሞ ድምፃቸውን ማሰማት የጀመሩት ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ገደማ ጀምሮ ነው።

በሺዎች የሚቆጠሩ በመቐለ የሚገኙ ተፈናቃዮች ዛሬ በከተማዋ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያካሂዱ "ወደ ቤታችን መልሱን" ፣ "የፕሪቶርያ ውል ይከበር" ፣ "መንግስት ረስቶናል" ፣ "እኛም ዜጎች ነን" የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮች በተፈናቃዮቹ ተስተጋብተዋል። ሰልፈኛ ተፈናቃዮቹ ሕወሓት እና የኢትዮጵያ መንግስት በፕሪቶሪያ የደረሱት ስምምነት እየተገበሩ አይደለም በማለት ቅሬታቸው የገለፁ ሲሆን ዓለምአቀፍ ለጋሾችም የርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች የተካፈሉበት የመቐለ የተቃውሞ ሰልፍ
መነሻቸውን በመቐለ የሚገኙ የተለያዩ መጠልያ ጣብያዎች እና ሌሎች አካባቢዎች ያደረጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮችምስል Million Haileselassie/DW

ከተፈናቃይ ሰልፈኞቹ መካከል ያነጋገርናቸው ከሶስት ዓመት በላይ ለሚሆን ግዜ የከፋ ሕይወት እየመሩ መሆኑ በማንሳት፥ የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ አስተዳደር ወደቦታቸው እንዲመልሷቸው ጠይቀዋል።

ሌላው ጦርነቱ በ2013 ዓመተምህረት ሲቀሰቀስ «ከምዕራብ ትግራይ» የተፈናቀሉት እና አሁን በመቐለ ሰብዓ ካሬ መጠልያ የሚኖሩ አዛውንት ተፈናቃይ ተስፋይ ገብሩ፥ ተፈናቃዮ በዘላቂነት ወደ ቦታው ከመመለስ በዘለለ እስከዛው አስፈላጊ ድጋፍ ሊደረግልን ይገባል ይላሉ።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር  በይፋ ይቅርታ ጠይቋል
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ተፈናቃዮች ያበትን ሁኔታ እንደሚረዳ በመግለጥ ለሰልፈኞ በይፋ ይቅርታ ጠይቋልምስል Million Haileselassie/DW

ሰልፈኞቹ በሕወሓት ጽሕፈት ቤት እና የክልሉ አስተዳደር ፊት በመሰባሰብ ቅሬታቸው አሰምተዋል። ሰልፈኞቹ በክልሉ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት በነበራቸው ቆይታ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት ምላሽ ተሰጥቷቸው። ተፈናቃዮች በአስከፊ ሁኔታ ላይ እንዳሉ አስተዳደራቸው እንደሚገነዘብ የተናገሩት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ "ፌደራል መንግሰት ሥራውን ስላልሠ፣ በእኛ በኩልም የሚጠበቅብን ጥረት ማድረግ ሲገባን ባለማድረጋችን" ችግሩ ወደከፋ ደረጃ መድረሱ በመግለፅ ለዚህም "ይቅርታ" ጠይቀዋል። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተፈናቃዮች ጥያቄ ለመመለስ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚሰራም ተናግረዋል።

በዚህ ጉዳይ ዙርያ ከኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት የመንግስት ባለስልጣናት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ