1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መቅደስ ገ/መድህን፤ ቲክቶክ እንድጽፍ፤ እንዳነብ አግዞኛል

ሰኞ፣ ሰኔ 17 2016

ቲክቶክ በተለይ አሁን አሁን ወጣቱን ትዉልድ ረድቷል፤ ብዙ ሰዉም ተቀይሮበታል። ጥሩ መድረክ ነዉ ማለት እችላለሁ። ችሎታ ያለዉ መድረክ ላይ መቅረብ ያልቻለ ሰዉ በቲክቶክ ችሎታዉን ሊያሳይ እና ተቀባይነትን ሊያገኝ ይችላል። ገንዘብም መስራት ይቻላል። ግን የቲክቶክ አጠቃቀም በጥንቃቄ መሆን አለበት። ወደ አልባሌ ሊወስድም ይችላል።

https://p.dw.com/p/4hPlC
The 24-year-old Mekedes Gebremedehin- Well-known poet and Tiktoker from Ethiopia
ምስል Mekedes Gebremedin

መቅደስ ገ/መድህን፤ ቲክቶክ እንድጽፍ እንዳነብ አግዞኛል

መቅደስ ገ/መድህን፤ ቲክቶክ እንድጽፍ እንዳነብ አግዞኛል 

  "በቲክቶክ መድረክ ጽሑፎቼን አቅርቤ ብዙ ተከታዮችን ብሎም ልምዴን እንዳጠነክር እንዳሻሽል አድርጎኛል"  የምትለንን የሥነ-ጽሑፍ ባለሞያ ወጣትን ያስተዋዉቀናል።  

መቅደስ ገ/መድህን ትባላለች የ 24 ዓመት ወጣት ናት፤ ሥነ-ግጥም ሥነ-ጽሑፍ በአጠቃላይ ህይወትዋ ነዉ።
«መቅደስ መቅደስ ገ/መድህን እባላለሁ የ 24 ዓመት ልጅ ነኝ። በብዛት ግጥም ነዉ የምጽፈዉ። የሰዎችን ግጥም እና ሥነ-ጽሑፍንም አነባለሁ። በአሁኑ ወቅት በባንክ ቤት በመደበኛነት ሰራተኛ ነኝ።»  
እህቶች አሉኝ እኔ ግን ታናሻቸዉ ነኝ። የቤቱ ትንሽ ልጅ እኔ ነኝ።  ትምህርቴን ጨርሼ የባንክ ሰራተኛም ነኝ። ግን ሥነ-ጽሑፍ መክሊቴ ነዉ። ከስራ በኋላ የምዝናናናበት እራሴን የማስተምርበት ስትል መቅደስ ገ/መድህን አጫዉታናለች። 


«በእርግጥ ግጥሞችን የምፅፈዉ ሰዎች የኔን ግጥም ከመጀመርያዉ ላይ ሲያነቡት አልያም ሲያዳምጡት፤ ይሄ ነዉ ብለዉ ሲያነቡ የነበረዉ ሳይሆን በመጨረሻዉ ግጥሙ መልዕክቱ፤ ሌላ ሆኖ ሲያልቅ እንዲደነቁ ወይም እንዲገረሙ አድርጌ ነዉ የምጽፈዉ። ስለዋሽንትም የፃፍኩት መጀመርያ፤ ሰዉ ሌላ ሌላ ሊያስብ ይችላል ግን መጨረሻ ስለዋሽንት መጻፌን አሳይቼ ነዉ የቋጨሁት። እና ይህ እራሱ አንድ ጥበብ ፤ አንድ የኪነጥበብ ብቃት ነዉ።» 
ወጣት መቅደስ በቅርቡ አንድ ዋሽንትን በማስመልከት የጻፍሽዉን ግጥም አስመልክቶ በርካታ ቀልብን ስቦ እንደነበር በተለያዩ ማህበራዊ መገናኛዎች እንዲሁም በአገር ዉስጥ መገናኛ ዘዴዎች ቀርበሽ ስለ ግጥምሽ፤ እና ስለተሰጥኦሽ አሳይተሻል።  

መቅደስ ገ/መድህን፤ ቲክቶክ እንድጽፍ እንዳነብ አግዞኛል
መቅደስ ገ/መድህን፤ ቲክቶክ እንድጽፍ እንዳነብ አግዞኛል ምስል Mekedes Gebremedin


«ስለ ዋሽንት የጻፍኩትን ያደመጡም ሆኑ ያነበቡ የሰጡኝ አስተያየቶች ባለጌ ምንድነዉ እንዲህ አይነት ጽሑፍ የምትጽፊዉ ብለዉ ነዉ ትችት ያቀረቡት። በብዛት ነገሩን በመጥፎ የተረዱ ሰዎች ነበሩ። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ደስ ይላል። አዳምጬ እስክጨርስ ፤ በመጨረሻ ይህ ይመጣል ብዬ አላሰብኩም ነበር፤ ብለዉ ያበረታቱኝም አሉ። አንዳንዶች፤ሲያገኙኝ  ስለዋሽንት በጻፍኩት ግጥም ስያሜ «ይንፉሽ ይነፋፉሽ»  ብለዉ የሚጠሩኝ ነበር። አንዳንዶች ደግሞ ከግጥሙ መሃል የፈለጉትን ብቻ ለይተዉ አዉጥተዉ ቪዲዮ የሰሩብኝ እና ስሜንም ያጠፉ፤ እንደዉም የወረደ ነገር የተናገሩም አሉ።» 


ገጣሚ መቅደስ ገ/መድህን፤ ሥነ-ጽሑፎችሽን ግጥሞችሽን ምንግዜ ነዉ የምትጽፊያቸዉ? እንደነገርሽኝን የባንክ ሰራተኛ ነሽ፤ ብዙ ጊዜ ቲክቶክ ላይ እናይሻለን፤ ሥነ-ጽሑፍ እና ሥነ-ግጥም በሚደመጥበት ቡድን ዉስጥ ብዙ ተከታዮች ያዳምጡሻል ፤ እና መቼ ነዉ የሥነ-ጽሑፎችሽ ጊዜ ያለሽ? የቲክቶኩንስ መንደር እንዴት ትገልጭዋለሽ?  ግን ይህ የቲክቶኩ መንደር ጥቅሙ ምን ያህል ነዉ?

መቅደስ ገ/መድህን፤ ቲክቶክ እንድጽፍ እንዳነብ አግዞኛል
መቅደስ ገ/መድህን፤ ቲክቶክ እንድጽፍ እንዳነብ አግዞኛል ምስል Mekedes Gebremedin


«ሥነ-ግጥሞቼን የምጽፋቸዉ ከስራ ሰዓት በኃላ ምሽት ላይ ነዉ። ማታ የምጽፈዉ ስራዩን ላለመበደል እና ሥራዩ የመኖርያዬ መሰረታዊ ምንች ስለሆነ ነዉ። ከስራ ወደ ቤቴ ስመለስ ግን ሥነ ግጥም መፃፍ ካለብኝ እጽፋለሁ ማንበብ ካለብኝ ቁጭ ብዬ አነባለሁ። የቲክቶክ መንደር ለኔ ጥሩ እይታ ነዉ የሆነኝ። እራሴን ለማዉጣት ከሕዝብ ጋር ለማገናኘት፤ ለራሴም ቢሆን መክሊቴን ለመኖር እንዳነብ እንድጽፍ ያደረገኝ ቲክቶክ ነዉ። ቲክቶክ ለኔ ጥሩ ነዉ ያደረገልኝ። ወደ 280 ሺህ ተከታዮች አሉኝ። በቅርቡ ዩቲዮብም ከፍቻለሁ፤ በዩቲዩብም እየመጣሁ ነዉ። ስለዋሽንት ግጥምን ከመጻፊ በፊት ሰዎች ጋር ያለኝ ግንኙነት ጥሩ ነበር ከዋሽንቱ ግጥም በኋላ ግን የተለያዩ ስሜቶችን ሰምቻለሁ። እንደሚታወቀዉ አማርና ሰይጣን ቋንቋ ነዉ ይባላል። እና እንደ ትርጓሚ ወስደዉት ነዉ። በፈለጉት መንገድ ተረድተዉት ነዉ እኔን በራሳቸዉ ሚዛን ላይ ያስቀመጡኝ። በሌላ በኩል እራሱን ግጥሙን ለሌሎች ሰዎች እያዳረሱ እራሱ ታዋቂ ለመሆን የፈለጉም ነበሩ።» 

ቲክቶክ
ቲክቶክምስል Marijan Murat/dpa/picture alliance


„ተይዉ ፖለቲካን ዝም ብለሽ ሳሚኝ „ ከሚለዉ ከገጣሚ ደሱ ፍቅርኤል ስነ መድብል ወጣት መቅደስ ገ/መድሕን በጥሩ ተዉኔታዊ አነባበብ አቅርባልናለች። 
ወጣት መቅደስ እንደዉ ከባህልም አንጻር ሴትም በመሆንሽ ከቤተሰቦችዋ የደረሰባት ይህ ነዉ የሚባል ጫና የለም። የቲክቶኩን ዓለም ተሞክሮዋም እንዲህ አካላናለች። 

መቅደስ ገ/መድህን፤ ቲክቶክ እንድጽፍ እንዳነብ አግዞኛል
መቅደስ ገ/መድህን፤ ቲክቶክ እንድጽፍ እንዳነብ አግዞኛል ምስል Mekedes Gebremedin


«ቲክቶክ በተለይ አሁን አሁን ወጣቱን ትዉልድ ረድቷል፤  ብዙ ሰዉም ተቀይሮበታል። ጥሩ መድረክ ነዉ ማለት እችላለሁ። ችሎታ ያለዉ መድረክ ላይ መቅረብ ያልቻለ ሰዉ በቲክቶክ ችሎታዉን ሊያሳይ እና ተቀባይነትን ሊያገኝ ይችላል። ገንዘብም መስራት ይቻላል። ግን የቲክቶክ አጠቃቀም በጥንቃቄ መሆን አለበት። የሰዉ ልጅ አደባባይ ሲወጣ ችግርም ሊደርስበት ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል። ቴክቶክ ብዙ እዉቀት የሚታይበት የሚደመጥበት ብዙ ሰዎችን የሚተዋወቁበት መድረክ እንደመሆኑም መጠን አጠቃቀሙን ላላወቀዉ ቲክቶክ በተለይ ወጣቱን ስራ ፈት ሊያደርግ ይችላል፤ ወደ አልባሌም ሊወስድ ይችላል። ሁሉን ነገር በብልሃት መያዝ አስፈላጊ ነዉ። » 

አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ