መቀሌን ጨምሮ የትግራይ ከተሞች በአሸንዳ ደምቀዋል
ሐሙስ፣ ነሐሴ 16 2016ማስታወቂያ
መቐለ በአሸንዳ ደምቃለች። ሺዎች የሚቆጠር እንግዳ ለአሸንዳ በዓል ወደ መቐለ ገብቷል። አሸንዳ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀን በድምቀት የሚከበር ሲሆን ከባህልዊ እና ሃይማኖታዊ ትውፊቱ በዘለለ ኢኮኖሚያዊ ትርጉሙም ትልቅ ሆኗል።
የተሳተፉበት ያሉ፣ ከጦርነቱ በኃላ መቐለ ጨምሮ ሌሎች ከተሞች ያነቃቃው የአሸንዳ በዓል አካባቢ ከዛሬ ጀምሮ በመቐለ በድምቀት መከበር ጀምሯል። ከተማዋ በባህላዊ ትርኢቶች፣ የሴቶች ጭፈራ እና ዘፈን፣ ጥበብ ደምቃለች።
በዚህ በየዓመቱ ከነሐሴ 16 ማለትም ፆመ ፍልሰታ መጠናቀቅ በኃላ ለተከታታይ ሶስት ቀን የሚከበር በዓል፥ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የመጡ እንግዶችም ታደመውበታል።
እየደመቁ የመጡት የልጃገረዶች እና ሴቶች በዓላት
በከተማው ካለው ደማቅ ድባባ፣ በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ የሚከፈልባቸው የሙዚቃ ድግሶች እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ውጪ የሆነ ሁነት ደግሞ በሌላው የመቐለ ክፍል መመልከት ይቻላል። በመቐለ ሰብዓ ካሬ በተባለው የተፈናቃይ መጠልያ ያሉ ሴቶች በዓሉ እንደሌሎች በቤታቸው እያከበሩ አይደሉም።
ሁለት መልክ የያዘው በዓል በአብዛኛው የትግራይ ከተሞች መከበር ጀምሯል።
ታምራት ዲንሳ
ሚሊዮን ኃይለስላሴ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር