ተሻሽሎ የፀደቀው አዋጅ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 1 2013ማስታወቂያ
በሁለት ክልሎች ወይም በፌዴራልና በክልሎች መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን ለመፍታት፣ ክልሎች ችግሩ እንዲፈታ ካልጠየቁ ፣ሆኖም ችግሩ ከቀጠለ የፌደሬሽን ምክር ቤት በራሱ ተነሳሽነት መፍትሔ እንዲፈልግ የሚፈቅድ የተሻሻለ አዋጅ ፀደቀ። ነባሩ አዋጅ ሁለቱ ወገኖች ካልተስማሙ በአንድ ወይም ሁለቱ ወገኖች በሚቀርብ ጥያቄ ምክር ቤቱ ለጉዳዩ መፍትሔ እንዲሰጥ ቢደነግግም በተግባር የመፍትሔ እርምጃ ሳይወስድ ቆይቷል።የሕዝብ ተወካዮች ምክር ትናንት ያፀደቀው አዋጅ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አሁን እየቀረቡ ካሉ የሕዝብ ፍላጎቶችና ጥያቄዎች አንፃር፣ በሕገ መንግሥቱ የተሰጡትን ተልዕኮዎች በቀልጣፋና በውጤታማ መንገድ ለመፈጸም በሚያስችለው ሁኔታ ላይ ባለመገኘቱ የተሻሻለ ነው ተብሏል።በማሻሻያ አዋጁ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የሕግ ባለሙያ መንግሥት በቅርብ ጊዜ ሕገ መንግሥታዊ አተረጓጎም ሥርዓቱን የሚመለከተውን የሕገ መንግሥት ክፍል የማሻሻል ውጥን እንደሌለው አመላካች ነው ብለዋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ