1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለትግራይ ችግር ተቃዋሚዎች ህወሃትን ከሰሱ

ሐሙስ፣ መጋቢት 1 2014

እየቀጠለ ባለው ጦርነት ምክንያት በትግራይ ያለው ህዝብ ለከፋ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር መጋለጡ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ። ለችግሩ መባባስም ህወሃትን ተጠያቂ አድርገዋል።

https://p.dw.com/p/48Hvi
Äthiopien Tigray-Provinz Mekele
ምስል EDUARDO SOTERAS/AFP

ለትግራይ ችግር ተቃዋሚዎች ህወሃትን ከሰሱ

እየቀጠለ ባለው ጦርነት ምክንያት በትግራይ ያለው ህዝብ ለከፋ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር መጋለጡ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ። ፓርቲዎቹ መፍትሔ ባለማበጀት እና ተጨማሪ ችግር በመፍጠር ትግራይን እያስተዳደረ ያለው በህወሓት የሚመራው ክልላዊ መንግስት ወቅሰዋል። በትግራይ ያለው ረሀብ፣ የማሕበራዊ አገልግሎቶች እጦት እና ሌሎች ችግሮች በአጭር ግዜ መፍትሔ ካላገኙ በቅርቡ አስከፊ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል የገለፁት በትግራይ የሚንቀሳቀሱት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፖርቲዎች፥ ዓለም ያለው ሁኔታ በትክክል ተገንዝቦ የትግራይ ህዝብ ችግር የሚያሳጥር ጫና ይፍጠር ብለዋል።

ሚሊየን ኃይለ ሥላሴ

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ