1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሃምሳ በመቶ የሚከፈልበት ሐዋላ በትግራይ

ሐሙስ፣ ጥር 18 2015

`` ያው መጀመሪያ 40%, 50% እየከፈልን ነበር የምንክከው። እሱም ይድረስ አይድረስ አይታወቅም። አንድአንድ ጊዜ በከሃዲዎች እተበላ ነበር። አሁን ደግሞ ባንክ ተጀመረ ተብሎ እስከ 2,000 ብር እየተሰጠ ነበር። አሁን ደግሞ ብር የለንም ብለው አስቁመውታል።``

https://p.dw.com/p/4Mib6
Äthiopien Emperor Yohannes IV Mekelle, Tigray
ምስል Million Haileselassie/DW

ሃምሳ በመቶ የሚከፈልበት ሐዋላ በትግራይ

በትግራይ ከሰላም ስምምነቱ ቦኋላ ተከፍተው የነበሩ ባንኮች መልሰው ስራ በማቆማቸው የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ከዚህ ቀደም በደላላ ይልኩበት ወደነበረው የአላላክ ዘይቤ ለመመለስ መገደዳቸውን ገልጸዋል። ከስምምነቱ በፊት ለደላሎች ከላኩት ብር ግማሽ ያህሉ እየተቆረጠ ለቤተሰቦች ይደርስ እንደነበር ያስታወሱት ተገልጋዮቹ አሁን ደግሞ ባንኮች የብር ኖት አልቆብናል በሚል አገልግሎት መስጠት በማቆማቸው ወደ ቀድሞው የደላላ የሃዋላ አገልግሎት መመለሳቸውን ተናግረዋል።
አቶ ረዘነ በርሀ ነዋሪነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የትግራይ ክልል ተወላጅ ናቸው። እሳቸው በስራ ምክንያት አዲስ አበባ ቢኖሩም አብዛኛው ቤተሰቦቻቸው ትግራይ ውስጥ ይኖራሉ። ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ የባንክ፣ የስልክና ሌሎች አገልግሎቶች በመቋረጣቸው ወደቤተሰብ ገንዘብ የሚልኩበት ሕጋዊ መንገድ አልነበራቸውም። በማጠያየቅ በደላላ በኩል ቢያገኙም ማንነቱ በማያውቁት ሰው በኩል መቶ ሺህ ከፍለው ሃምሳ ሺህ ለቤተሰብ እንዲደርስ ተስማምተው ላኩ። እናም ደረሰ። በየጊዜው በዚህ መልኩ ቢልኩም ሁሌ ፋሲካ የለም እንደሚባለው አንዳንዴም የላኩት ገንዘብ ለቤተሰብ ሳይደርስ አልያም ወደ ላኪው ሳይመለስ በሳቸው አገላለጽ ተበልቶ ይቀር ነበር።`` ያው መጀመሪያ 40%, 50% እየከፈልን ነበር የምንክከው። እሱም ይድረስ አይድረስ አይታወቅም። አንድአንድ ጊዜ በከሃዲዎች እተበላ ነበር። አሁን ደግሞ ባንክ ተጀመረ ተብሎ እስከ 2,000 ብር እየተሰጠ ነበር። አሁን ደግሞ ብር የለንም ብለው አስቁመውታል። በተለይ ንግድባንክ ብር የለኝም ብሎ አጀመረም። ወጋገን ጀምሮ ነበር አሁን ብር የለኝም ብሎ አቁሟል።``አሁን ደግሞ ባንክ ተጀመረ ተብሎ እስከ 2,000 ብር እየተሰጠ ነበር። አሁን ደግሞ ብር የለንም ብለው አስቁመውታል። በተለይ ንግድባንክ ብር የለኝም ብሎ አጀመረም። ወጋገን ጀምሮ ነበር አሁን ብር የለኝም ብሎ አቁሟል።``
አቶ ሐዱሽ ዲበኩሉም የዚሁ ሐዋላ ተጠቃሚ ነበሩ። የሰላም ስምምነቱን መሰረት ተደርጎ ባንኮች ስራ ጀምረዋል ቢባልም ሁለት ወር ሳይሞላቸው ብር ጨርሰናል በሚል ምክንያት አገልግሎት በማቆማቸው የለመለመው ተስፋቸው እንደተሟጠጠ ገልጸውልናል።
`` ከቤተሰብ የሚላክልን ገንዘብ በደላሎች በኩል ከ40 እስከ 50 በመቶ እየከፈልን ነበር የምንቀበለው። በዚህ ምክንያት ሕብረተሰቡ ከባድ ችግር እያሳለፈ ነበር። አሁን ደግሞ ሰላም ስምምነቱ መሰረት ባንኮች ተከፍተው እስከ 2ሺሕ አንዳንዶቹም እስከ 5 ሺህ ብር በሀዋላ የተላከልህ ገንዘብ ማውጣት ይቻል ነበር።ይህ አገልግሎት ግን ከሁለት ሳምንት በላይ መሄድ አልቻለም።``በጀርመን ሃገር የፍራንክፈርት ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ጽጋብ ሐድጉም እሳቸውና ቤተሰቦቻቸው የዚሁ ሰለባ መሆናቸውን አጫውተውናል።
ሁሎም ባንኮች በመከፈታቸው ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት፣ ብራቸውን አንቀሳቅሰው እራሳቸውን ለማገዝ የነበራቸውን ተስፋ ባንኮች ብር ጨርሰናል ብለው የተጀመረችውን ውሱን አገልግሎት በማቆማቸው ምክንያት እንደቀድሞው እስከ ሃምሳ በመቶ ባይሆንም አሁንም ከ15 እስከ ሃያ በመቶ የአገልግሎት ክፍያ እየተቆነደዱ ለመላክ መገደዳቸውን ገልጸውልናል። የፌደራል መንግስት  ተጨባጭ መፍትሔ እንዲሰጣቸው በመማጸን።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ታምራት ዲንሳ

Äthiopien Tigray | Hauptstadt Mekele
ምስል MICHAEL TEWELDE/AFP/Getty Images
Part of Mekelle city | Mek'ele / Äthiopien
ምስል Million Hailesllassie/DW