ሰኞ፣ ሚያዝያ 28 2016-የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ወታደራዊ ዘመቻን ለመጀመር ወደ 100 ሺህ የሚሆኑ የራፋህ ነዋሪዎች አካባቢዉን ለቀዉ እንዲወጡ አዘዘ።
-የአዉሮጳ ህብረት የዉጭ ጉዳይ ተጠሪ ጆሴፕ ቦሬል እስራኤል በራፋህ የሚገኙ ሲቪል ነዋሪዎች እንዲለቁ ትእዛዝ ማስተላለፏ ሁኔታዉን አስከፊ ያደርገዋል ሲሉ አሳሰቡ። የዮርዳኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸዉ በፍልስጤማዉያን ላይ ሌላ እልቂት እያንዣበበ ነዉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
-በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና አገልጋዮቿ ላይ የሚደረገው "ማሳደድና እስር በአስቸኳይ ይቁም" ሲል እናት ፓርቲ ጠየቀ።
-ቻድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እያካሄደች ነው።