Eshete Bekeleሰኞ፣ መጋቢት 16 2016የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በጋዛ የተኩስ አቁም ላይ እንዲደረስ ጥሪ አቀረበ። የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሔደው ምርጫ ለመሳተፍ የመመዝገቢያ 50,000 ዶላር ክፈሉ መባላቸውን ተቃወሙ። በሴኔጋል ሥልጣን ላይ የሚገኘውን ጥምር ፓርቲ ወክለው ለፕሬዝደንትነት የተወዳደሩት አማዱ ባ የተቃዋሚ ፓርቲው ዕጩ ማሸነፋቸውን አምነው ተቀበሉ። የአሜሪካው አውሮፕላን አምራች ቦይንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዴቪድ ካልሁን ከኃላፊነታቸው እንደሚለቁ አስታወቀ። የሩሲያ ፍርድ ቤት ከሞስኮ ወጣ ብሎ በሚገኘው ክሮከስ አዳራሽ ጥቃት ፈጽመው 137 ሰዎች በመግደል የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች እስር ቤት እንዲቆዩ አዘዘ።