Eshete Bekeleሰኞ፣ ግንቦት 12 2016ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት አካውንት 6 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ለማጭበርበር ሞክረዋል በሚል በቁጥጥር ሥር ከዋሉ ተጠርጣሪዎች መካከል አራቱ አሁንም በፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ ፍርድ ቤት አዘዘ። የወላይታ ዞን የሠራተኞቹን ደሞዝ ከሚቀጥለው ዓመት ተበድሮ ለመክፈል መገደዱ ተገለጸ። የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የጦር መሳርያ ዝውውርን ለመቆጣጠር እየጣረ መሆኑን አስታወቀ። በኦሮሚያ ክልል በምትገኘው ኪረሙ ከተማ 50 ሺሕ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን የምሥራቅ ወለጋ ዞን ገለጸ። የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ለእስራኤልና ፍልስጤም የሁለት መንግሥት መፍትሔ ለማስገኘት እየሰሩ መሆናቸውን አስታወቁ