1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

DW Amharic የሰኔ 22 ቀን 2016 የዓለም ዜና

Eshete Bekeleቅዳሜ፣ ሰኔ 22 2016

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የፋኖ ታጣቂዎች የሚያደርጉትን “የርስ በርስ ጦርነት” አቁመው ድርድር እንዲጀምሩ በአማራ ክልል የተቋቋመ የሰላም ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ። “የርስ በርስ ጦርነቱን በድርድር ለመፍታት ፈቃደኛ ነኝ” ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት “ብዙ አደረጃጀት እና መሪ” አላቸው ያላቸው የፋኖ ታጣቂዎች “ለመደራደር አንድ መሆን አለባቸው” በማለቱ ምክር ቤቱ መቋቋሙን ተገልጿል። • የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች የሱዳን “ሰው ሰራሽ ረሐብ” ከተፈራው የከፋ ሊሆን እንደሚችል አስጠነቀቁ። በኬንያ ተቃውሞ ቢያንስ 30 ሰዎች መገደላቸውን ሒውማን ራይትስ ዎች አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/4hfkH
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ስለዚሕ ዝግጅት

ስለዚሕ ዝግጅት

PODC-DW-Amharisch-News-DWcom

የዓለም ዜና

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና የዜና ትንታኔዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ።