1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

DW Amharic ነሐሴ 20 ቀን 2016 የዓለም ዜና

ሰኞ፣ ነሐሴ 20 2016

DW Amharic--በስለት ሦስት ሰዎች የተገደሉባትን ዞሊንገን የጀርመን ምዕራባዊ ከተማን ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ እና ታዋቂ የሃገሪቱ ፖለቲከኞች ለህዝብ አጋርነታቸዉን በማሳየት ከተማዋን ጎበኙ። IS የተባለዉ ጽንፈኛ ቡድን ሃላፊነት በወሰደበት በዚህ ጥቃት ሦስት ጀርመናዉያን ተገድለዋል፤ ስምንት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። --በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በደረሰ ናዳ ህይወታቸው ካለፈ 10 ሰዎች መካከል እስካሁን የስድስቱን አስከሬን ማግኘት እንዳልተቻለ ተገለፀ። በሌላ በኩል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ ደቡብ አሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ፤ በኦሞ ወንዝና በቱርካና ሀይቅ ሙላት በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቀሉ።

https://p.dw.com/p/4jwV8
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ስለዚሕ ዝግጅት

ስለዚሕ ዝግጅት

PODC-DW-Amharisch-News-DWcom

የዓለም ዜና

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና የዜና ትንታኔዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ።