AGOA ለአፍሪቃ የቀረበዉ የንግድ እድል6 ነሐሴ 2001ረቡዕ፣ ነሐሴ 6 2001ከሰሃራ በስተደቡብ የሚገኙ የአፍሪቃ ሀገራት ከቀረጥና ኮታ ነፃ ሸቀጦች ወደአሜሪካ እንዲያስገቡ የሚፈቅደዉ AGOA በመባል በእንግሊዝኛ ምህፃር የሚታወቀዉ ዉልን የተመለከተ ስምንተኛ ጉባኤ ባለፈዉ ሳምንት ኬንያ ናይሮቢ ላይ ተካሂዷል።https://p.dw.com/p/J8VZየኦባማ ቪዲዮ መልዕክትምስል APማስታወቂያ መስፈት አሟልተዉ የዚህ ዉል ተጠቃሚ የሆኑ የአፍሪቃ ሀገራትና አሜሪካ በየጊዜዉ እየተገናኙ ይመክራሉ። በዚህኛዉ ጉባኤ ላይ አዲሷ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን የንግድ ልዑካንን አስከትለዉ ተሳትፈዋል። AGOA ለአፍሪቃ ሀገራቱ ጠቀሜታ እንዳለዉ ብዙዎች ቢናገሩም አሜሪካም ጥሬ አላባ የምታገኝበት መንገድ ነዉ የሚሉት አልጠፉም። አበበ ፈለቀ/ሸዋዬ ለገሠ