60ኛ ዓመት ዶይቸ ቬለ -የአድማጮች አስተያየት
ግብፃዊው አህመድ
« ትምህርቴን በጀርመን ሀገር ለመከታተል ስለወሰንኩ፡ ቀኑን ሙሉ የዶይቸ ቬለን ቲቪ ማየት ጀምሬአለሁ። »
አልጀሪያዊው ቤዛዝል ፌርሀት፡
« ዶይቸ ቬለን አደምጣለሁ። ምክንያቱም በዓለም ካሉት የውጭ ሀገር ራድዮ ጣቢያዎች መካከል ምርጡ እሱ በመሆኑ። ዶይቸ ቬለ በጀርመን ሀገር ስላለው ሁኔታ ትክክለኛውን ሥዕል ያቀርባል። እኔ ዶይቸ ቬለን ጀርመንን፡ አውሮጳን እና መላውን ዓለም የሚያሳይ ክፍት መስኮት አድርጌ እመለከተዋለሁ። »
የጋናው ተወላጅ ኤማኑዌል፡
« የዶይቸ ቬለን ፕሮግራም ብቻ ሳይሆን የምወደው፡ የዶይቸ ቬለ ሰራተኞች አድማጮች እና ተጠቃሚዎች ለሚያቀርቡዋቸው ጥያቄዎች ፈጥነው መልስ የሚሰጡበትን እና ባጠቃላይ ለኛ የሚያሳዩትንም ልዩ አቀራረብ ጭምር ነው። »
የቶጎው ተወላጅ ኢብራሂም፡
« እኔ ለወደፊቱ የምመኘው ለአፍሪቃ ብቻ ልዩ የዶይቸ ቬለ አገልግሎት እንዲጀመር ነው። »
ሞሮኳዊው ሙስጠፋ፡
« ስለዶይቸ ቤለ መጀመሪያ ያወቁት የሁለተኛ ደረጃ የጀርመንኛ ቋንቋ ተማሪ በነበርኩበት እአአ በ1987 ዓም ነበር። ያኔ ማታ ማታ የዶይቸ ቬለን ሥርጭት አደምጥ ነበር፤ ምንም እንኳን ከሚተላለፈው ዝግጅት መካከል ይገባኝ የነበረው ከሁለት እስከ አምሥት ከመቶው ብቻ ቢሆንም። »
ናይጀሪያዊው መሀመድ፡
« ለኔ ፣ ዶይቸ ቬለ ማለት ከሌሎች ሀገራት ጋ በአጭር የሞገድ መስመር እና በኢንተርኔት የሚያገናኝ ተቋም ማለት ነው። »
የቤኒንዋ ተወላጅ ፕሩደንስ፡
« ዶይች ቬለ ወደፊት የጀርመናውያኑ ዕውቀት ማሸጋገሪያ ተቋም ምልክት በመሆን ልክ « ሜድ ኢን ጀርመኒ » በመባል ጥሩ ስም እንዳተረፈው የጀርመን ምርት ዕውቅና እንዲያገኝ እመኛለሁ። ባለፉት ሦስት አሠርተ ዓመታት በተከታተልናቸው የዶይች ቬለ ዝግጅቶች አማካኝነትም አዘውትረው ዘረኞች ናቸው ስለሚባሉት ጀርመናውያን የነበረንን መጥፎ አስተያየት ለመቀየር ችለናል። »
ታንዛንያዊው ራስ ፍራንስ፡
« ዶይች ቬለ ዜና እና መረጃዎችን ለእኛ ተጠቃሚዎቹ ለማድረስ የሚያደርገውን ትልቅ ጥረት በተለይ አደንቃለሁ። »
አልጀሪያዊቷ ሳዱ፡
«ዶይቸ ቬለ የሚያቀርባቸው የፕሮግራም አገልግሎቶች ከሌሎቹ ራድዮ ጣቢያዎች ወይም ድረ ገፆች የተለየ በመሆኑ ነው የምጠቀምበት። ዶይቸ ቬለ በሚያበረክተው ልዩ ስራው ሁሌ ያስደስተኛል። ዶይች ቬለ በፈጠራ ችሎታው በመጠቀም የውይይት እና ተባብሮ የመስራቱን መንፈሥ ማነቃቃት ተሳክቶለታል። »
የጊኒው ተወላጅ ሳምባዲዩማ፡
« እርግጥ፡ ወደ አፍሪቃ ሥርጭት የሚያስተላልፉ ብዙ የራድዮ ጣቢያዎች አሉ። ነገር ግን፡ የናንተን ጣቢያ ከሌሎቹ ልዩ የሚያደርገው ተጠቃሚዎችን በቀጥታ የሚያሳትፍበት አሰራሩ ነው።»
ጋናዊው ሣሙኤል፡
« በዶይቸ ቬለ አገልግሎት የምጠቀመው ጣቢያው ወቅታው ዜና ስለሚያቀርብ እና ሰራተኞቹንም ብቃት ያላቸው ናቸው ብዬ ስለማምን ነው ።»
ግብፃዊው ሻዲ፡
« በዶይቸ ቬለ አገልግሎት የምጠቀመው ታማኝ እና ትክክለኛ ዘገባዎችን የሚያቀርብ ግሩም የማሰራጪያ ጣቢያ በመሆኑ ነው። »