1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ2015 አበይት ክንዉኖች

Mohammed Negashሰኞ፣ ጳጉሜን 6 2015

ለወትሮዉ የአፍሪቃ ሕብረትንና ሕብረቱ የሰየማቸዉን አደራዳሪዎችን ለኢትዮጵያ መንግስት የሚወግኑ በማለት የሚቃወማዉ፣ በርካታ ቅድመ ሁኔታዎችን ሲደርድር የነበረዉም ሕወሓት ወይም የትግራይ መከላከያ ኃይል በያኔዉ አዲስ ዓመት አዲስ አቋም የያዘዉ በጦር ሜዳዉ ዉጊያ ክፉኛ ሥለተመታ ነዉ የሚሉ ብዙዎች ነበሩ።አሉም

https://p.dw.com/p/4WDDd

የኢትዮጵያዉያኑ 2015 ዓመት፣ የሠላም ጥሪ ደምቆ የተሰማበት፣ የሰላም ድርድር አግባቢ ዉጤት- ክሽፈትም የታየበት፣ጦርነት ቆሞ ጦርነት የተጫረበት፣ አንድ የነበሩ መስተዳድሮች የተከፋፈሉበት የኃይማኖት መሪዎች ተጣልተዉ የታረቁበት-የተለያዩበትም ዓመት ነዉ።በጦርነት፣ግጭት የሞተ-የተፈናቀለዉ ተቆጥሮ ሳያበቃ በነባርና አዳዲስ ግጭቶች ሌሎች የሞቱ-የተፈናቀሉበት፣ ፖለቲከኞች የተገደሉበት፣ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል የመሆንዋ በጎ መሰል ዜና በሸቀጥ ዋጋ ንረት የታጠፈበት፣የፀጥታ መናጋት፣ ድርቅና ረሐብ የሚሊዮኖችን መከራ ያጠናበት ዓመትም ነዉ። የቀድሞ ባልደረባዬ ዘዉዱ ታደሰ ዘመን-ዘመንን ሲተካ ቀሪዉ ታሪክ ነዉ-እንዳለዉ ሆኖ 2015 በነበር የሚዘከርበትን የጎሉ ጉዳዮችን ባጭጭሩ ጠቃቅሰን እንሰናበታዉ።ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ስለዚሕ ዝግጅት

ስለዚሕ ዝግጅት

DW-Interview mit Frank-Walter Steinmeier
ምስል DW/R. Oberhammerምስል DW/R. Oberhammer

ማሕደረ ዜና

ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀርብበታል። አዘጋጅ፣ ነጋሽ መሐመድ