1434ኛ የኢድ አል አድሐ በዓል
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 5 2006ማስታወቂያ
በበዓሉ አከባበር ወቅት እንደወትሮው በርካታ አማኞች በስፍራው አለመገኘታቸውን እና በቀዘቀዘ ሁኔታ መጠናቀቁንን ከዚያ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ የበዓሉን ስነ ስርዓቱን ተከታትሎ አጭር ዘገባ ልኮልናል።
እንዲሁ የአዲስ አበባ ወኪላችን ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሔር ወደ መርካቶ አካባቢ ተዘዋውሮ አንድ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኝ ቤተሰብን ጎብኝቷል። በዓሉን እንዴት እንዳከበሩ ዘገባው ያስቃኘናል።
ሌላው ዘገባ ደግሞ የእስልምና እምነት ተከታዮች ቢችሉ በህይወት ዘመናቸው አንዴ የሚጓዙበት መካ ወደምትገኝበት ሳውዲ አረቢያ ይወስደናል። ዘንድሮም በሀጅ ፀሎት ላይ ለመሳተፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያን ወደ ሳውዲ አረቢያ ተጉዘዋል። በዓሉን እንዴት አከበሩት? ምንስ ገጠማቸው? የጅዳ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ተከታትሎታል።
እነዚህን ሶስት ዘገባዎች ማድመጥ ይችላሉ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነብዩ ሲራክ
አርያም ተክሌ