12 ተኛው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር እና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 12 2001ማስታወቂያ
ትናንት ምሽት ልማደኛው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የአስር ሺህ ሜትሩን ውድድር በ26 ደቂቃ 46.31 ሰከንድ በአንደኝነት ጨርሷል ። ቀነኒሳ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና በ 10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ሲያሸንፍ የትናንቱ ለአራተኛ ጊዜ መሆኑ ነው ። እ.ጎ.አ በ 2003 ፓሪስ ፈረንሳይ ላይ ፣ በ2005 ሄልሲንኪ ፊንላንድ እንዲሁም በ2007 ኦሳካ ጃፓን የተካሄዱት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና የ 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች አሸናፊ ቀነኒሳ በቀለ ትናንትም ለአራተኛ ጊዜ አንደኛ ወጥቶ የወርቁን ሜዳልያ አጥልቋል ። ኤርትራዊው ዘረሰናይ ታደሰ ደግሞ ሁለተኛ ወጥቷል ። የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል የቀነኒሳን ድል መነሻ አድርጎ በኢትዮጵያ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት በሚደረገው ጥረት ላይ ያተኮረ ዘገባ አጠናቅሯል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል ፣ ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ