ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ለህትመት ያለመብቃትዋ
ማክሰኞ፣ መስከረም 8 2005ማስታወቂያ
ከአንድ አመት ግድም በፊት መታተም የጀመረችዉ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ በብርሃነ እና ሰላም ማተምያ ቤት ለመጀመርያ ግዜ ለህትመት ስትበቃ ከ 2500 በማይበልጥ ቅጂ እንደነበር ተነግሮአል። ቀስ በቀስ አንባቢዎችዋን የሳበችዉ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ በስተ- መጨረሻ 20,000 ያህል ቅጂ እንደሚታተም የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ግን ጋዜጣዋ ለህትመት ሳትበቃ አንባብያንም እጅ ሳትደርስ ከቀረች ሶስት ሳምንት እንደሆናት ተመልክቶአል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሃንስ ገ/እግዚአብሄር ስለ ጋዜጣዉ ለህትመት ያለመብቃት ጉዳይ ዘገባ አጠናቅሮአል።
ዮሃንስ ገ/እግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ