ፈረንሳይ ውስጥ የተቀጣጠለው ተቃውሞ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 1 2012ማስታወቂያ
በፈረንሳይ አዲሱን የጡረታ ሕግ በመቃወም የሚደረገዉ አድማ ቀጥሏል። የፕሬዝደንት ኢማኑዌል ማክሮ መንግሥት በመላው ሀገሪቱ የሥራ ማቆም አድማ እና ተቃውሞ የቀሰቀሰውን የዚህን ሕግ ይዘት ለማስረዳት እየጣረ ነው። በትናንትናው ዕለት በፓሪስ ጎዳናዎች በርካቶች ለተቃውሞ የወጡ ሲሆን የሕዝብ መጓጓዣ አገልግሎቶች የሥራ ማቆም አድማው ያነጣጠረባቸው እንደሆነ እና ይህም ለሳምንታት ይቀጥላል የሚል ስጋት መኖሩን ዘገባዎች ያመለክታሉ። አዲሱ የጡረታ ሕግ ከጎርጎሪዮሳዊው 1975 ዓ,ም ወዲህ የተወለዱ እስከ 64 ዓመት ከሠሩ ብቻ ሙሉ የጡረታ ገንዘብ ሊያገኙ እንደሚችሉ ሲያመለክት፤ ከዚያ በፊት ያሉት በ62 ዓመታቸው ይህን ደረጃ እንደሚያገኙ መግለፁ በሀገሪቱ ከፍተኛ ተቃውሞ ቀስቅሷል። የፓሪሷ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ ዘገባ ልካልናለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ