ፀረ ሙስና ትግል
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 30 2011ማስታወቂያ
የፀረ ሙስና ትግል በዘመቻና የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲባል መካሄድ እንደሌለበት አንድ ምሁር አሳሰቡ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ እና የሰብዓዊ መብት መምህር ዶክተር ጌታሁን ካሳ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ትግሉ እውነተኛ እና ችግሩን በትክክል ለማስወገድ የሚካሄድ ሊሆን ይገባል። ዶክተር ጌታሁን ጥንታዊ ጽሁፍ ያቀረቡበት ፣የፌደራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ቪዥን ኢትዮጵያ ኮንግረስ ፎር ዴሞክራሲ ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበር በቅርቡ ያዘጋጀዉ ዐውደ ጥናት በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ ነበር። ዐውደ ጥናቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ