ጥቃትና መፈናቀል በአማሮ ልዩ ወረዳ
ዓርብ፣ ግንቦት 6 2013ማስታወቂያ
በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌያት የታጠቁ ሀይሎች ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ ከስድስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከአካባቢያቸው ተፈናቀሉ። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ነዋሪዎቹ ከትናንት ጀምሮ አካባቢያቸውን እየለቀቁ የሚገኙት ትናንት ለሊት ወደ መንደሮቹ ዘልቀው የገቡ ታጣቂዎች ሁለት ሰዎችን ገድለው ሌሎች ሁለት ማቁሰላቸውንና የመኖሪያ ቤቶችን ማቃጠላቸውን ተከትሎ ነው። ታጣቂዎች በየጊዜው በልዩ ወረዳው ነዋሪዎች ላይ የሚደርሱት ጥቃት እየተባባሰ ይገኛል የሚሉት የወረዳው ባለስልጣናት በበኩላቸው የክልሉ መንግስት ለችግሩ መፍትሄ ሊሰጥ አልቻለም ሲሉ ወቅሰዋል ።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ