1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጎርፍ ያፈናቀላቸው በጋምቤላ

ሐሙስ፣ መስከረም 21 2013

በጋምቤላ ክልል በጎርፍ የተጎዱ አካባቢ ነዋሪዎች እ|የተሰጠን ያለው እርዳታ በቂ አይደለም ሲሉ ተናገሩ፣ የክልሉ መንግሥት ለዕለት እርዳታ የሚውል 5 ሚሊዮን ብር መመደቡን የጋምቤላ ክልል መንግሥት አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3jIRw
Äthiopien | Stadt Gambella
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

«ከፍተኛ የምግብ ርዳታ ያስፈልጋል»

በጋምቤላ ክልል በጎርፍ የተጎዱ አካባቢ ነዋሪዎች እ|የተሰጠን ያለው እርዳታ በቂ አይደለም ሲሉ ተናገሩ፣ የክልሉ መንግሥት ለዕለት እርዳታ የሚውል 5 ሚሊዮን ብር መመደቡን የጋምቤላ ክልል መንግሥት አስታውቋል። በክልሉ ያሉ መንግሥታዊ  ያልሆኑ ድርጅቶች የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት እየተረባረቡ እንደሆነ ደግሞ የክልሉ አደጋ መከላከል መሥሪያ ቤት አመልክቷል።  በክልሉ 30 ሺህ ያህል ህዝብ በጎርፍ ምክንያት መፈናቀልና ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የጋምቤላ ክልል መንግሥት በአፋር በጎርፍ ለተፈናቀሉ ወገኖች አንድ ሚሊዮን 500 ሺህ ብር እርዳታ አድርጓል። ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ በጋምቤላ ክልል የሚገኙ ወንዞች ሞልተው ባስከተሉት ጎርፍ በርካታ ህዝብ ከመኖሪያ ቤቱ የተፈናቀለ ሲሆን ለከፍተኛ የምግብ እርዳታ መጋለጡን የጋምቤላ ክልል አደጋ መከላከል መሥሪያ ቤት አስታውቋል። መሥሪያ ቤቱ ጉዳቱን ከገመገመ በኋላ ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው እርዳታ እየሰጠ እንደሆነ ገልጧል። ከባሕር ዳር ዓለምነው መኮንን ዝርዝር ዘገባ አለው።

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ