1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግጭት ጦርነት ያጠላበት ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ

እሑድ፣ ሰኔ 2 2016

ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የሃይማኖት ሰዎችና ዜጎች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በሚታሰሩበት፤ በኦሮሚያ እና አማራ ክልል ከመንግሥት ኃይሎች የታጠቁ ኃይሎች በይፋ በሚዋጉበት በዚህ ወቅት እንዴት ያለ ሀገራዊ ምክክር ነው የሚካሄደው በማለትም ይሞግታሉ።

https://p.dw.com/p/4gnyu
 ሀገራዊ ምክክር ባለፈው ሳምንት መጀመሩ ይፋ ሆኗል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን ለሐገራዊ ምክክሩ ማስተዋዋቂያ ካሰራጫቸዉ መልዕክቶች አንዱምስል Seyoum Getu/DW

ግጭት ጦርነት ያጠላበት ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ

ለረዥም ጊዜያት በተስፋ የተጠበቀው ሀገራዊ ምክክር ባለፈው ሳምንት መጀመሩ ይፋ ሆኗል። በመንግሥት ከተሰየመ ሁለት ዓመታትን ያስቆጠረው ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን «ኢትዮጵያ እየመከረች ነው» በሚል መሪ ቃል አዲስ አበባ ላይ ለሰባት ቀናት ያካሄደው መድረክ የመወያያ አጀንዳዎችን ለመለየት የመጀመሪያው ምዕራፍ ነው ብሏል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የሄደው ችግር መነሻው ፖለቲካዊ ነው የሚሉ ወገኖች ምንም እንኳን ሀገራዊ ምክክር መታሰቡን ቢደግፉም ሂደቱ ላይ ጥያቄዎችን በማንሳት አንዳንዶቹ እራሳቸውን ማግለላቸውን በይፋ እያሳወቁ ነው።

ከኮሚሽኑ አመሰራረት አንስቶ የገዢው ፓርቲ ጣልቃገብነትን አጥብቀው የሚተቹትም መድረኩ አካታችነት ይጎድለዋል በሚል ከወዲሁ አዎንታዊ ውጤት እንደማይጠብቁ ይገልጻሉ።

ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የሃይማኖት ሰዎችና ዜጎች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በሚታሰሩበት፤ በኦሮሚያ እና አማራ ክልል ከመንግሥት ኃይሎች የታጠቁ ኃይሎች በይፋ በሚዋጉበት በዚህ ወቅት እንዴት ያለ ሀገራዊ ምክክር ነው የሚካሄደው በማለትም ይሞግታሉ። ግጭት ጦርነት ያጠላበት ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ የዚህ ሳምንት የዶቼ ቬለ የእንወያይ ርዕሰ ጉዳይ ነው። 

ሸዋዬ ለገሰ