ግጭት እና እስራት በጋሞጎፋ ዞን9 ሐምሌ 2005ማክሰኞ፣ ሐምሌ 9 2005በደቡብ ክልል ጋሞጎፋ ዞን ቁጫ ወረዳ የማንነት፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎችን ያነሱ ከሁለት መቶ የሚበልጡ ሰዎች መታሰራቸውንhttps://p.dw.com/p/199GFማስታወቂያ እና አንዳንዶችም እንደተጎዱ የታሳሪዎች ቤተሰቦች እና ባካባቢው የሚንቀሳቀሱ አንድ ፖለቲከኛ ለዶይቸ ቬለ ገለጹ። የክልሉ የፍትሕ ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ለዶይቸ ቬለ እንዳስታወቁት፣ ግጭቱ በሕገ ወጥ መንገድ በተደራጀ ሰልፍ ወቅት ነው የተፈጠረው። ጉዳዩም በመጣራት ላይ ይገኛል። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር አርያም ተክሌ ነጋሽ መሀመድ