1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትኢትዮጵያ

በሰሜንና ምዕራብ ጎጃም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በግጭት ምክንያት ለፈተና አይቀመጡም

ቅዳሜ፣ ሰኔ 1 2016

በሰሜን ጎጃም እና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች የሚገኙ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች የዘንድሮውን ብሔራዊ ፈተና እንደማይወስዱ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ ተናገሩ። አካባቢዎቹ የመንግሥት ኃይሎች እና የፋኖ ታጣቂዎች የሚዋጉባቸው ናቸው። በክልሉ ከ350 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና የሚቀጠመጡ ቢሆንም ዕድሉን ያላገኙ ብዙ ናቸው።

https://p.dw.com/p/4golN
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ “ሰሜን ጎጃምና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ምንም ተማሪ አያስፈትኑም” ሲሉ ተናግረዋል። ምስል Alemnew Mekonnen/DW

ግጭት ባለባቸው የሰሜን ጎጃም እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተና አይቀመጡም

ዘንድሮ በሚሰጠው የ6ኛና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የክልልን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በምዕራብና ሰሜን ጎጃም ዞኖች እንደማይሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። ለብዙ ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና አዲሱን የትምህርት ስርዓት ተከትሎ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚጥ ቢሮው አመልክቷል፡፡

የ6ኛና የ8ኛ ክፍል  ክልል አቀፍ ፈተና ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ ፈተናው መኒሰጥባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች መሰጠት ይጀምራል፡፡

የ6ኛና 8ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ በአማራ ክልል የሚሰጥ ሲሆን የክልሉ ወቅታዊ የሰላም ሁኔታ ችግር በፈጠረባቸው የምዕራብና ሰሜን ጎጃም ዞኖች አንድም ተማሪ እንደማይፈተን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡

ቻግኒ ከተማ ዉስጥ በተደረገ የተኩስ ልዉዉጥ ሰዎች መገደላቸዉ የቀሰቀሰዉ ዉዝግብ

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ ዛሬ የፈተና አሰጣጡን በማስመልከት በቢሯቸው በሰጡት መግለጫ ወቅታዊ ጉዳዩ በፈጠረው ሁኔታ በምዕራብና በሰሜን ጎጃም ዞኖችና በምስራቅ ጎጃም በከፊል ፈተናው አይሰጥም ብለዋል፡፡

“ምንም ዓይነት ተማሪ የማያስፈትኑ ሁለት ዞኖች አሉ፣ ሰሜን ጎጃምና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ምንም ተማሪ አያስፈትኑም፣ 6ም፣ 8ም 12ኛም አያስፈትኑም፣ ምስራቅ ጎጃም የተወሰነ ያስፈትናል፣ ይህ ዘመኑን ያልዋጀ ነገር ነው፣ ያልተማሩ ተማሪዎች ስነልቦናቸው ስለሚጎዳ ስልጣናና ማካካሻ ትምህርት እንዲወስዱ እናደርጋለን” ብለዋል፡፡

ፈተናው በሚሰጥባቸው ሌሎች ዞኖች ደግሞ ከ350ሺህ በላይ የ6ኛና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ዶ/ር ሙሉነሽ ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2016 በጀት ዓመት 6.2 ሚሊዮን ተማሪዎች ለመመዝገብ አቅዶ የነበረ ቢሆንም 2.6 ሚሊዮን እንዳልተመዘገቡ አስታውቋል። ምስል Alemnew Mekonnen/DW

“በዚህ ዓመት ፈተናው በሚሰጥባቸው አካባቢዎች 8ኛ ክፍል በቁጥር ወደ 184 ሺህ 393 ተማሪዎች፣ በ3ሺህ 209 ትምህርት ቤቶች ሰኔ 4 እና 5/ 2016 ዓ ም ፈተናው ይሰጣል፣ 6ኛ ክፍል ደግሞ 170ሺህ 470 ተማሪዎች በ4ሺህ 355 ትምህርት ቤቶች ሰኔ 13 እና 14/2016 ዓ ም ፈተናቸውን ይወስዳሉ” ነው ያሉት። 

የመንገድ መዘጋት በምዕራብና በምስራቅ ጎጃም ዞኖች

እንደኃላፊዋ፣ 3 ዓይነት ተማሪዎች በክልሉ ነበሩ ብለዋል፡፡ ትምህርት አቋርጠው የነበሩ፣ በተወሰነ እየተቆራረጠ የተማሩና ምንም ልተማሩ ናቸው ነው ያሉት፤  ትምህርት ሳይማሩ የቆዩ ተማሪዎች ከጓደኞቻቸው ወደ ኋላ እንዳይወቀሩ በተለያዩ መንገዶች የማማካካሻ ትምህርት እንደሚሰጥ በመግለጫቸው አመልክተዋል፡፡

በአማራ ክልል መመዝገብ ከነበረባቸው 6.2 ሚሊዮን ተማሪዎች መካከል 2.6 ሚሊዮን የሚሆኑት ወደ ትምህርት ቤት እንዳልመጡ፣ 350 የአንደኛና 225 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስራ እንዳልጀመሩ በመጋቢት 2016 ዓ ም የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉነሽ ገልፀው እንደነበር ይታወሳል፡፡

አንድ አመት እየሞላው ያለውና በአማራ ክልል የተከሰተው የፀጥታ መታወክ በክልሉ ሰብአዊ፣  ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ቀውስ ፈጥሯል፡፡

ዓለምነው መኮንን

እሸቴ በቀለ