ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና አወዛጋቢዉ የጉዞ እገዳ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 12 2010ማስታወቂያ
ነገ አምስተርዳም ላይ በሚካሄደዉ ክብረ በዓል ላይ የኔዘርላንዱን ንጉስ ቪለም አልክሳንደርን ጨምሮ የሃገሪቱ ባለሥልጣናትና የድርጅቱ ተጠሪዎች እንደሚገኙበት ተነግሮአል። ከጥቂት ሰዓታት በፊት አዲስ አበባ ላይ በስልክ ያገኘነዉ ጋዜጠኛና የመብት ተቆርቋሪዉ እስክንድር ነጋ ትናንት ምሽት ጉዞዉን ሲታገድ የተነጠቀዉ ፓስፖርቱ ዛሬ ከቀትር በኋላ እንደተመለሰለት ተናግሮአል። መጓዝም እንደሚችል ተነግሮኛል ብሎአል። ጋዜጠኛ እስክንድር ትናንት አዉሮፕላን ማረፍያ ያጋጠመዉን በመዘርዘር ይጀምራል።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ