ኤልያስ እና ዳንኤል በዋስ እንዲለቀቁ ተፈረደ
ሰኞ፣ ሐምሌ 10 2009ማስታወቂያ
ዛሬ ያስቻለው የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና ፖለቲከኛ ዳንኤል ሺበሺ በዋስ እንዲለቀቁ ፈረደ። ችሎቱ የስር ፍርድ ቤት፣ የፍርድ ሂደቱ በዝግ እንዲታይ የሰጠውን ብይን በተመለከተ ለምስክሩ ጥበቃ ሲባል በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን አጽድቋል። በዚሁ መሠረትየአቃቤ ህግ ምስክር የሆኑት አንድ የደህንነት አባል ዛሬ በዝግ ችሎት መመስከራቸውን የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘግቧል.
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ