ገጣሚ ማርታ ሐይለእየሱስ
ዓርብ፣ መጋቢት 21 2004ማስታወቂያ
ማርታ ግጥሞቿ በተለያዩ ጭብጦች ላይ እንዳተኮሩ ትናገራለች። ለምሳሌ በፍቅር፣ በሀገር፣ በማህበራዊ ነገሮች ላይ እና በሌሎችም ርዕሶች ላይ፤ እሷም እንደገጣሚ እነዚህ ጉዳዮች ወሳኝ ናቸው ትላለች። ማርታ እስካሁንም ከ50 የሚበልጡ ግጥሞች ፅፋለች።
የ24 ዓመቷ ማርታ ግጥም የመፃፍ ፍላጎቱና ዝንባሌው ያላቸው ወጣቶች ይህንኑ ችሎታቸውን ለማዳበር ጠንክረው ቢሰሩ መልካም እንደሚሆን ታምናለች። እንደሷ ግጥምን በት/ቤት ብቻ ሳይሆን በትርፍ ሰዓታቸውም እንዲፅፉ እና የቋንቋ ችሎታቸውን በት/ቤት እንዲያሳድጉም ትመክራለች። ይህንን አላማቸውን ከግብ ለማድረስ መደረግ ይኖርበታል ስለምትለው ማርታ ታስረዳለች። ከግጥሞቿ ሁለቱን እንዲሁም ከኢትዮጵያዊ የቀድሞ እና ያሁን ገጣሚያን የማን አድናቂ እንደሆነች ጭምር የገለፀችልንን ማድመጥ ይቻላል።
ልደት አበበ
አርያም ተክሌ