1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

ዶናልድ ትራምፕ ላይ የመግደል ሙከራ አድራጊው ምን ሆነ?

አበበ ፈለቀ
ረቡዕ፣ መስከረም 8 2017

የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከዳግመኛ የመግደል ሙከራ ከተረፉ በኋላ የወደፊት የደሕንነታቸው ሁኔታ አነጋጋሪ ሁኗል ። የድያ ሙከራ በተደረገበት የጎልፍ መጫወቻ ሥፍራቸው ያለው ደሕንነት ምን ያህል ጥብቅ መሆኑን ጠባቂዎቻቸውን ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/4kl1L
Donald Trump Attentat USA Ryan Routh Verdächtiger
ምስል ASSOCIATED PRESS/picture alliance

የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከዳግመኛ የመግደል ሙከራ ከተረፉ በኋላ የወደፊት የደሕንነታቸው ሁኔታ አነጋጋሪ ሁኗል ። የድያ ሙከራ በተደረገበት የጎልፍ መጫወቻ ሥፍራቸው ያለው ደሕንነት ምን ያህል ጥብቅ መሆኑን ጠባቂዎቻቸውን ጠይቀዋል።  ለመሆኑ የግድያ ሙከራ አድራጊው የ58 ዓመቱ ግለሰብ ላይ ምን አይነት የክስ ሒደት ተከፈተ?  የቀድሞው ፕሬዚደንት  በሁለት ወራት ጊዜያት ብቻ ሁለት ጊዜ የግድያ ሙከራ  እንዴት ሊፈጸምባቸው ቻለ?

ትናንት ወደምርጫ ዘመቻቸው የገቡት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የከሸፈው ሁለተኛ የግድያ ሙከራ ከሰሞሙ የተደረገው ፍሎሪዳ በሚገኘው የዶናልድ ትራምፕ ጎልፍ መጫወቻ ሜዳ ውስጥ ተደብቆ በነበረው የ58 ዓመት ተጠርጣሪ ነበር ። ተጠርጣሪው አጥር ስር ተደብቆ በቅርብ ርቀት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ሲያነጣጥር  የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጠባቂዎች (ሴክሬት ሰርቪስ) አባላት ተኩስ ተከፍቶበታል ። ወደ ተሽከርካሪው ሮጦ ለማምለጥ ቢሞክርም በቁጥጥር ሥር ውሏል። ራየን ዌስሊ ሩዝ የተባለው ተጠርጣሪ የጦር መሣሪያ አነጣጥሮ ዶናልድ ትራምፕን ይጠባበቅ እንደነበር የአሜሪካ ባለሥልጣናት ገልጠዋል ። ሰውዬው ዌስት ፓልም በሚገኘው የጎልፍ መጫወቻ ሥፍራ ምግብ እና መሣሪያ ይዞ ለ12 ሰዓታት ግድም መቆየቱ የጥበቃ ሁኔታው አሳሳቢ ነው አስብሏል ።

የቀድሞው ፕሬዚደንት ለምርጫ ዘመቻ ወደ ሚቺጋን ማቅናታቸው ተዘግቧል ። የዴሞክራቲክ ፓርቲ ተወካይዩዋ ተቀናቃኛቸው ካማላ ሐሪስም በበኩላቸው ወደ ፔንሲልቫኒያ ለምርጫ እንዳቀኑ ተጠቅሷል ። 

ዶናልድ ትራምፕ ላይ በሁለት ወራት ጊዜያት ግድም ሁለተኛ የመግደል ሙከራ መደረጉ ግን እጅግ አነጋግሯል ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ፀሐይ ጫኔ