ድብቅ እስር ቤቶች በትግራይ
ረቡዕ፣ ኅዳር 12 2011ማስታወቂያ
ሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ መስተዳድር በተለያዩ አካባቢዎች የድብቅ ወይም ሕገ-ወጥ እስር ቤቶች አሉ መባሉ የተለያዩ ወገኖችን እያወዛገበ ነዉ።ምክትል ርዕሠ-መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረ-ሚካኤል በቅርቡ በሰጡት መግለጫ «ድብቅ እስር ቤት» የሚባል እንደለሌ አስታዉቀዉ ነበር።አረና ለሉዓላዊነት እና ዴሞክራሲ የተባለዉ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ግን ትግራይ ርዕሠ-ከተማ መቀሌ ዉስጥ ቢያንስ አንድ የድብቅ እስር ቤት መኖሩን እንደሚያዉቁ ተናግረዋል።በትግራይ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ተጠሪ በበኩላቸዉ የድብቅ እስር ቤት ሥለመኖሩ የደረሰን ጥቆማ የለም ባይ ናቸዉ።
ሚሊዮን ኃይለስላሴ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ