1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ ምዕራብ ሸዋ የከፋው የግጭት ተጽእኖ እንዲቆም፤ ግልጽ ደብዳቤ

ሐሙስ፣ መስከረም 2 2017

የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ነዋሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጻፉት ደብዳቤ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች 79 ሰዎች መገደላቸውን ገለጹ። ነዋሪዎቹ ለኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች ጭምር እንዲደርስ እንፈልጋለን ባሉት ደብዳቤ “ከታጣቂዎቹ ወግነዋል” በሚል ክስ የ21 ሰዎች ቤቶች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መቃጠላቸውን አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/4kYMs
China | Seidenstraßengipfel
ምስል Ken Ishii/REUTERS

ደቡብ ምዕራብ ሸዋ የከፋው የግጭት ተጽእኖ እንዲቆም፤ ግልጽ ደብዳቤ

በኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በኦሮሚያው የተራዘመ ግጭት-ጦርነት ክፉኛ ከተጎዱ አከባቢዎች አንዱና ዋነኛው ተጠቃሽ ነው፡፡ በዚህ አከባቢ በተወሳሰበው ግጭት በየጊዜው ሰዎች ይገደላሉ፤ አርሶ አደር - ነጋዴዎች ተቀምጦ ማረስ ብሎም ነግዶ ማትረፍ ብርቱ ፈተና የሆነባቸውም ወረዳዎች በርካቶች ናቸው፡፡

ታዲያ በዚህ የተማረሩት ስለጉዳዩ አሳሰብን ያሉ በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ ያሉት የአከባቢው ተወላጆች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ በየደረጃው ላሉ ለክልልና ፌዴራል ባለስልጣናት እንዲሁም በውጊያው ውስጥ ላለው ለአሮሞ ነጻነት ሰራዊት አዛዦች እንዲደርስ ያሉትን ግልጽ ደብዳቤ ጽፈዋል፡፡

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተብሎ የተጻፈው ይህ ግልጽ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም፣ ለኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት እንዲሁም ለኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነሰ) አዛዦችም ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የግልጽ ደብዳቤው ጭብጥም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በተለይም በቀርሳ ማሊማ፣ ሶዶዳጪ እና ሰደን ሶዶ ወረዳዎች በኦሮሞ ህዝብ ላይ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎችም ሆነ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ተዋጊዎች ይፈጸማል ያሉት የንጹሃን ግድያ፣ መፈናቀል እና የንብረት ውድመት እንዲቆም የሚጠይቅ ነው፡፡

ስማቸውን ከመግለጽ ተቆጥበው አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ የሰጡ ጉዳዩ አሳሰበን ካሉ የአከባቢው ተወላጆች አንዱ በአለከባቢው በህዝብ ላይ ይደርሳል ያሉት በደልና ጉዳት በይፋ እንዲታወቅና እልባት እንዲፈለግለት ማሰባቸውን ነው የገለጹት፡፡

“በዋነኛነት መልእክታችንን ማስተላለፍ የፈለግነው ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ነው” ያሉት አስተያየት ሰጪው፤ “ህዝብ ስገደል፤ ስፈናቀል መንግስት አልተከላከላቸውም” በማለት ቅሬታቸውን አንስተዋል፡፡ ለገበሬው በነዚህ አከባቢዎች በህይወት መቆየት ቅንጦት ሆኖበታልም ብለዋል አስተያየት ሰጪው ደብዳቤውን ለአገሪቱ መሪ ለመጻፍ ያስገደዳቸውን ሁኔታ ስዘረዝሩ፡፡

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን እየከፋ የመጣው የንፁሃን ግድያ

አስተያየት ሰጪው አከሉ፡፡ ከዚህ በፊት እነዚህ አከባቢዎች ባላቸው ብርቱ የወል የሆነው አብሮ የመኖር ደልብ ባህል ይታወቁ ነበር፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ያ ድልብ የማህበረሰቡ እሴት ከመፈተንም አልፎ እንግዳ ነገርን ማስተናገድ ጀመረ፡፡ አስቀድሞ ከሌላ ቦታዎች ታግተው የሚመጡ ሰዎች ተገድለው እረኞች የሰው ልጅ አስከሬን በየሜዳው ተጥለው መገኘት ጀመረ፡፡ በሌሎች አከባቢዎች ይፈጸሙ የነበረው እገታዎች እንዲያ እያለ አስከፊ ወደሆነ ደረጃም ተሸጋገረ ብለዋል፡፡

“ማንኛውም ገበረ እየታገተ ገንዝብ መጠየቅ ስጀምር አቅም ያለው ሰው ሁሉ መሰደድ ጀመረ፡፡ ጊዜው ስራዝም የመንግስት አካል መጥቶ ለታታቂው ተባበራችሁ ብሎ የሚጠረጥረውን ሁሉ ማሳደድ ይጀምራል፡፡ ህዝብ ግን ተገዶ እንጂ ፈቅዶ አልነበርም፡፡ እናም በአከባቢ ላይ የሆነውና እየሆነ ለው አስደንጋጭ ነው” ብለውታል፡፡

ኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን እርሻ
ደብዳቤውን ከጻፉ የአካባቢው ነዋሪዎች አንዱ ገበሬው “በሕይወት መኖር ቅንጦት” ሆኖበታል ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ምስል Seyoum Getu/DW

የሚፈጸሙ ግድያዎች እና የቤቶች ቃጠሎ

እንደ ግልጽ ደብዳቤው ዝርዝር ይዘት ማብራሪያ ሁለቱ ተፋላሚዎች ከጦርነቱ ውጪ ያለው ማህበረሰብ ላይ አንዱ ከሌላው ጋር ይሰራል በሚል ፍረጃ መግደል ማፈናቀል ንብረታቸውን ማውደም ጎልቶ ይስተዋላል ሲል ይዘረዝራል፡፡ ደብዳቤው በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ታጣቂዎች በስም የተዘረዘሩ 17 ንጹሃን ዜጎችን የመንግስት ሰራተኛ ዘመድ ስላላቸው ብቻ ገድለው ከ40 በላይ ከብቶቻቸውን ስዘርፉ፤ የመንግስት የጸጥታ ሰዎች በፊናቸው የታጣቂዎቹ ቤተሰቦች ቤት አቃጥለዋል ይላል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በሕቡእ ተጠርቷል የተባለው የእንቅስቃሴ ገደብ

ደብዳቤው በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት የተገደሉ 79 ሰዎችን ስዘረዝር ከፊሎቹን እስከነፎቶያቸው አስቀምጧል፡፡ ለታጣቂዎቹ ወግነዋል የተባሉ የ21 ሰዎች ቤቶች ደግሞ በመንግስት ጸጥታ ኃይሎች መቃጠላቸውን ይህ ደብዳቤ የተጎጂዎቹን ስም ዘርዝሯል፡፡ “ቁጥሩ ስማቸው የደረሰን ብቻ በመሆኑ እውነታው ከዚህ ከፋ ነው” ይላሉ ጉዳዩ አሳሰበን ያሉ የአከባቢው ተወላጆች፡፡

አስፈሪ ሁኔታ የፈጠረው የሰዎች እገታ ወንጀል

በግጭቱ ተጠቂ ያልሆነም የማህበረሰብ አካል አለመኖሩ ተመልክቷል፡፡ የደብዳቤውም መልእክት፤ “ከምንግስት ከፍተኛ ባለስልታናት በተጨማሪ ለኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አዛዦችም ነው” የሚሉት አስተያየት ሰጪው፤  “ብዙ ጊዜ የሚሰጡ ማስተባባያዎች ሊታዩ ይገባል” ሲሉ ሞግተዋል፡፡ “በተለይም የደብዳቤው መልእክት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ደርሰው አነስተኛ ትኩረት እንኳ ብሰጥ” ያሳሰባቸው ጉዳይ እልባት እንደሚያገኝም አስረድተዋል፡፡

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በተለያዩ ጊዜያት የሚሰጡ መግለጫዎች የሚፈጸሙ እገታና ዘረፋዎች ብሎም የንጹሃን ግድያዎች በታጣቂዎቹ እንደማፈጸሙ ይገልጻል፡፡ መንግስት በፊናው በግጭቱ ውስጥ ንጹሃን ኢላማ እንደማይደረጉ በመግለጽ፤ ለኦሮሚያው ግጭት ማብቂያ ሰላም ብቸኛው አማራጭ መንገድ መሆኑን ያነሳል።

ሥዩም ጌቱ

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ